ቀን 5/11/2013 ዓ.ም

ማስታወቂያ

ለሂሳብ/ኦዲት ባለሙያዎች በሙሉ

የኢትየጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ የባለሙያ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እድሳት ከሀምሌ 01 እስከ 30 ባሉት ጊዜያቶች ድረስ የመንግስት ፖርታል በሆነው eservices.gov.et በኩል እንደሚከናወን ይታወቃል ፡፡

ይሁን እንጂ የ2014 ዓ.ም የእድሳት ጊዜ በተለያዩ ምክንያቶች በወቅቱ ባለመጠናቀቁ እስከ ነሐሴ 30/2013 ዓ.ም ድረስ የተራዘመ መሆኑን እያሳወቅን አመልካቾች አገልግሎቱን ለማገግኘት በቅድሚያ ተገቢውን የእድሳት የአገልግሎት ክፍያ ብር 750.00 (ሰባት መቶ አምሳ ብር) እንዲሁም ለኦዲት ባለሙያዎች ብር 780.00 (ሰባት መቶ ሰማንያ ብር ብቻ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ በሂሳብ ቁጥር 1000393097667 በኩል በመፈጸም የባንክ ዲፖዚት ይዛችሁ መቅረብ ይጠበቅባችºል ፡፡

ደንበኞች በአካል መጥታችሁ የታደሰ የምስክር ወረቀታችሁን መቀበል የምትችሉት በአጭር የመልእክት ቁጥር 8181 በኩል መልዕክት ሲደርሳችሁ ብቻ ሲሆን አስፈላጊ ዋና ዋና ሰነዶችን ይዛችሁ መቅረብ እንዳለባችሁ ከወዲሁ እናሳውቃለን ፡፡

                                     ከሰላምታ ጋር

ለበለጠ መረጃ ፡0118121949