ለመንግስት የልማት ድርጅቶች የፋይናንስ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው የIFRS ስልጠና ተጠናቀቀ

የኢትዮጵያ የሒሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ ከፌዴራል መንግስት የልማት ድርጅቶች ለተውጣጡ 114 የፋይናንስ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች በሁለት ዙር ከመጋቢት 12-16/2014 እና ከመጋቢት 19-23/2014 ዓ.ም ድረስ በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

የስልጠናው ዋና ዓላማ የህዝብ ጥቅም ያለባቸው ሪፖርት አቅራቢ አካላት የሂሳብ መግለጫቸውን በFull IFRS መሠረት አዘጋጅተው ወደ ቦርዱ ማቅረብ እንዲችሉ የፋይናንስ ባለሙያዎችን አቅም መገንባት መሆኑ ተገልጿል፡፡

በስልጠናው መዝጊያ የቦርዱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሂክመት አብደላ እንደተናገሩት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ለአገሪቱ ኢኮኖሚ የሚያበረክቱት አሰተዋጽኦ ወሳኝ በመሆኑ በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ባለው IFRS የሪፖርት አቀራረብ ደረጃ ለመተግበር እንዲችሉ ስልጠናው መሰጠቱን ገልጸዋል፡፡

በዕለቱም የስልጠናው ተሳታፊዎች ስልጠናው በቂ ዕወቀት ባላቸው ባለሙያዎች የተሰጠ በመሆኑ በተቋማቸው የሚያዘጋጁትን የሂሳብ መግለጫ  በፋይናንስ ሪፖርት ደረጃዎች መሠረት  ለመስራት እንደሚያግዛቸው እና ስልጠናው ወቅቱን የጠበቀ መሆኑንም አክለው ገልጸዋል፡፡