ለሪፖርት አቅራቢ አካላት በሙሉ

              የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ

           Accounting and Auditing Board of Ethiopia

            ቦርዱ በፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ አዋጅ ቁጥር 847/2006 አንቀጽ 4 ንዑስ አንቀጽ 2/”መ” እና “ሰ” እንዲሁም በአዋጁ  አንቀጽ ቁጥር 53 ንዑስ አንቀጽ(2) በተሰጠው ስልጣን መሰረት  የሪፖርት አቅራቢ አካላትን  መለያ መስፈርት እና ምዝገባ መመሪያ ቁጥር የኢ/ሂ/ኦ/ቦ 804/2013 በማዘጋጀት የሪፖርት አቅራቢ አካላት እና የሂሳብ መግለጫቸው እየመዘገበ ይገኛል፡፡ ቦርዱ አለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ደረጃዎች (IFRS)፣የመካከለኛና አነስተኛ ድርጅቶች አለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ደረጃዎች(IFRS for SME) እና ለሺቪል ማኅበረሰብ  ድርጅቶችና ማህበራት የሚያገለግል አለም አቀፍ የፐብሊክ ሴክተር የሂሳብ አያያዝ ደረጃዎች (IPSAS) መተግበር ያለባቸውን  የሪፖርት አቅራቢ አካላት ለመመዝገብ እንዲቻል በተለያየ ጊዜ የግንዛቤ መስጨበጫ  መድረኮችን በማዘጋጀት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ በዚህም ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የሪፖርት አቅራቢ አካላት ተመዝግበው በተመዘገቡበት የሪፖርት አቀራረብ ደረጃዎች መሰረት የሂሳብ መግለጫቸው በማዘጋጀት እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡ ይሁን እንጂ ይመዘገባል ተብሎ ከሚጠበቀው ቁጥር አንጻር  ሲታይ ገና ብዙ ያልተመዘገበ የሪፖርት አቅራቢ አካል እንዳለ ከተሰበሰበው መረጃ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በመሆኑም በወጣው መመሪያ በወቅቱ ባለመመዝገብ  የሚያስከትለው ቅጣት ስላለ ማንኛውም የሪፖርት  አቅራቢ አካል ቦርዱ በመመሪያ ባስቀመጠው የመለያ መስፈርትና ትረሽ ሆልድ  መሰረት የሚመለከተው መሆኑን በማረጋገጥ በወቅቱ ባለመመዝገብ ከሚመጣ ቅጣትና ተጠያቂነት እራሳችሁንና ድርጅታችሁን እንድትጠብቁ እያሳሰብን ምዝገባን በተመለከተ ከታች የተዘረዘረው መረጃ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የሪፖርት አቅራቢ አካላት ምዝገባን በተመለከተ አጠቃላይ መረጃ

ሀ.  በቦርዱ በሪፖርት አቅራቢነት የተለዩ አካላት

1.የህዝብ ጥቅም ያለባቸው የሪፖርት አቅራቢ አካላት መለያ መስፈርት

1.1 ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የሪፖርት አቅራቢ አካላት ከተሰማሩበት የስራ ዓይነት    

     ወይም ባህሪ አኳያ የህዝብ ጥቅም ያለባቸው የሪፖርት አቅራቢ አካላት ናቸው፡፡

ሀ. የሚያወጡትን የግዴታ ምስክር ወረቀት ቁጥጥር በሚደረግበት የካፒታል ገበያ

ለግብይት ያዋለ ወይም ለማዋል በዝግጅት ላይ ያለ ማንኛውም ኩባንያ፤

ለ. ባንኮች፣ የመድን ሰጪ ተቋማት፣ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት፣ የካፒታል ዕቃ

ፋይናንስ ኩባንያዎች እና የፋይናንስ ተቋማት፤

ሐ. በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ በመንግስት ቁጥጥር ስር ያለ የልማት ድርጅት፤

መ. የአክሲዮን ማህበር፤

ሠ. በሚመለከተው የመንግስት አካል ቁጥጥር የሚደረግበት የጡረታ ወይም የፕሮቪደንት

ፈንድ የሚያስተዳድር እና ተመሳሳይ ተግባር የሚፈጽም ተቋም፤

ረ. የሕብረት ስራ ዩኒየኖች፤

ሰ. ቁጥጥር የሚደረግበት የሸማቾች ማህበር፤

ሸ. የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅትና የበጎ አድራጎት ድርጅት፤

ቀ. የኢትዮጵያ የምርት ገበያ አባላት፤

1.2. ከሪፖርት አቅራቢው አካል የአመታዊ ገቢ፣ የሀብት መጠን፣ የዕዳ መጠን እና የሠራተኞች ብዛት   

አኳያ ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት መስፈርቶች ውስጥ ቢያንስ ሁለቱን የሚያሟላ ማንኛውም የሪፖርት   

      አቅራቢ አካል የህዝብ ጥቅም ያለበት አካል ነው፡፡

ሀ. ዓመታዊ ገቢው ብር 300 ሚሊዮን (ሦስት መቶ ሚሊዮን) ወይም በላይ የሆነ፤

ለ. ጠቅላላ ሀብቱ ብር 200 ሚሊዮን (ሁለት መቶ ሚሊዮን) ወይም በላይ የሆነ፤

ሐ. ጠቅላላ ዕዳው ብር 200 ሚሊዮን (ሁለት መቶ ሚሊዮን) ወይም በላይ የሆነ፤

መ. የሠራተኞቹ ብዛት 200 (ሁለት መቶ) ወይም በላይ የሆነ፤

 1. አነስተኛና መካከለኛ ድርጅቶች መለያ መስፈርት

2.1 ከሪፖርት አቅራቢው አካል የአመታዊ ገቢ፣ የሀብት መጠን፣የዕዳ መጠን እና የሠራተኞች ብዛት

       አኳያ ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት መስፈርቶች ውስጥ ቢያንስ ሁለቱን የሚያሟላ ማንኛውም የሪፖርት  

       አቅራቢ አካል አነስተኛና መካከለኛ ድርጅት     

   ነው፡፡

ሀ. ዓመታዊ ገቢው ብር 20 ሚሊዮን (ሃያ ሚሊዮን) እና ከብር 300 ሚሊዮን (ሦስት

መቶ ሚሊዮን) በታች የሆነ፤

ለ. ጠቅላላ ሀብቱ ብር 20 ሚሊዮን (ሃያ ሚሊዮን) እና ከብር 200 ሚሊዮን (ሁለት

መቶ ሚሊዮን) በታች የሆነ፤

ሐ. ጠቅላላ ዕዳው ብር 20 ሚሊዮን (ሃያ ሚሊዮን) እና ከብር 200 ሚሊዮን (ሁለት

መቶ ሚሊዮን) በታች የሆነ፤

መ. የሠራተኞቱ ብዛት 20 (ሃያ) እና ከ200 በታች የሆነ፤

2.2. ከላይ በተራ ቁጥር 1.2 የተመለከተው የመጠን መስፈርት የሚያሟሉት እንደ ተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም  

        ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከላይ በተራ ቁጥር 2.1 የተመለከተው የመጠን መስፈርት ከግምት    

        ሳይገባ ወይም ባያሟላም በአነስተኛና መካከለኛ ድርጅት የሪፖርት አቅራቢነት ይመዘገባል፡፡

 ማሳሰቢያ

ከላይ በተራ ቁጥር 2.1 የተመለከተው የመጠን መስፈርት ውስጥ ሁለቱን የማያሟላና በሪፖርት አቅራቢነት የመመዝገብ ግዴታ የሌለበት የሽርክና ማህበር ወይም የግለሰብ የንግድ ድርጅት አዲሱ ትረሽ ሆልድ ከመውጣቱ በፊት የሂሳብ መግለጫው በአለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ደረጃዎች (IFRS) ወይም የመካከለኛና አነስተኛ ድርጅቶች አለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ደረጃዎች (IFRS for SME) አዘጋጅቶ የነበረ እንደሆነ በጀመረበት አለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ደረጃዎች መቀጠል አስፈላጊ መሆኑን እየገለጽን ከዚህ በፊት በነበረው ትረሽ ሆልድ መሰረት ተመዝግው ማዘጋጀት ያልጀመሩና ከዚህ በኃላም በፈቃደኝነት በመመዝገብ በፈለጉት አለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ደረጃዎች የሂሳብ መግለጫቸው ማዘጋጀት ይችላሉ፡፡

 ለ. ለምዝገባ አባሪ ሆነው መቅረብ ያለባቸው ሰነዶች/Essential Documents      

    for registration

 1. ግል ድርጅቶች/For Private Companies;

ነስተኛና መካከለኛ/ SME, የህዝብ ጥቅም ያለበት/PIE, የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አባል/ECX

1.1 ንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ቅጂ/Copy of Business Registration Certificate,

 • የንግድ ፍቃድ ሰርተፊኬት ቅጂ/Copy of Business License Certificate,
 • የመጨረሻ/ዓመታዊ የሂሳብ መግለጫ/Latest Annual Financial Report.
  • ኦዲት የተደረገ ከሆነ የኦዲት ድርጅቱ የሥራና የሙያ ፈቃድ ኮፒ አብሮ ይቀርባል፡፡
  • ኦዲት ያልተደረገና በውጭ ሂሳብ አዋቂ የተዘጋጀ ከሆነ የሂሳብ አዋቂ ድርጅቱ የሥራና የሙያ ፈቃድ ኮፒ አብሮ ይቀርባል፡፡
  • ኦዲት ያልተደረገና በውስጥ ሂሳብ ሠራተኛ የተዘጋጀ ከሆነ የሂሳብ ሠራተኛው የትምህርት ማስረጃና የፔሮል ኮፒ አብሮ ይቀርባል፡፡
 • የሥራ አስኪያጅ 3×4 የሆነ ፎቶ ግራፍ/Manager’s 3×4 size photograph
 1. የግል ድርጅት ላልሆነ/For Non-Private Companies

          ነስተኛና መካከለኛ/ SME, የህዝብ ጥቅም ያለበት/PIE, የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አባል/ECX,     

         የህብረት ስራ ዩኒየኖች/Cooperative Unions

2.1 ንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ቅጂ/Copy of Business Registration Certificate,

 • የንግድ ፍቃድ ሰርተፊኬት ቅጂ/Copy of Business License Certificate,

2.3 የመጨረሻ/ዓመታዊ የሂሳብ መግለጫ/ Latest Annual Financial Report.

2.3.1 ኦዲት የተደረገ ከሆነ የኦዲት ድርጅቱ የሥራና የሙያ ፈቃድ ኮፒ አብሮ ይቀርባል፡፡

2.3.2 ኦዲት ያልተደረገና በውጭ ሂሳብ አዋቂ የተዘጋጀ ከሆነ የሂሳብ አዋቂ ድርጅቱ

የሥራና የሙያ ፈቃድ ኮፒ አብሮ ይቀርባል፡፡

2.3.3 ኦዲት ያልተደረገና በውስጥ ሂሳብ ሠራተኛ የተዘጋጀ ከሆነ የሂሳብ ሠራተኛው

የትምህርት ማስረጃና የፔሮል ኮፒ አብሮ ይቀርባል፡፡

 • የመመስረቻ ጽሁፍ ቅጂ/Copy Article of Association,

2.5 የመተዳደሪያ ደንብ ቅጂ/Copy of Memorandum of Association,

2.6 የሥራ አስኪያጅ 3×4 የሆነ ፎቶ ግራፍ/Manager’s 3×4 size photograph

 1. ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች/For Civic Societies
 • የመጨረሻ/ ዓመታዊ የሂሳብ መግለጫ/ Latest Annual Financial Report.

3.1.1 ኦዲት የተደረገ ከሆነ የኦዲት ድርጅቱ የሥራና የሙያ ፈቃድ ኮፒ አብሮ ይቀርባል፡

3.1.2 ኦዲት ያልተደረገና በውጭ ሂሳብ አዋቂ የተዘጋጀ ከሆነ የሂሳብ አዋቂ ድርጅቱ የሥራና

የሙያ ፈቃድ ኮፒ አብሮ ይቀርባል፡፡

3.2.3 ኦዲት ያልተደረገና በውስጥ ሂሳብ ሠራተኛ የተዘጋጀ ከሆነ የሂሳብ ሠራተኛው የትምህርት

ማስረጃና የፔሮል ኮፒ አብሮ ይቀርባል፡፡

 • በተቆጣጣሪ መስሪያ ቤት የተሰጠው የምዝገባ ሰርተፊኬት ቅጂ/copy of Registration from the Regulatory body,
 • የመመስረቻ ጽሁፍ ቅጂ/ Copy of Article of Association,
 • የመተዳደሪያ ደንብ ቅጂ/Copy of Memorandum of Association,
 • የዋና ዳይሬክተር 3×4 የሆነ ፎቶ ግራፍ/General Director’s 3×4 size photograph

     3.6 በቢዝነስ ዘርፍ ላይ የተሰማራ ከሆነ በተጨማሪ/If it is a Business-oriented

 1. የንግድ ፍቃድ ሰርተፊኬት ቅጂ/Copy of Business License Certificate,
 2. ንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ቅጂ/Copy of Business Registration Certificate,
 3. ለመንግስት የልማት ድርጅቶች /For Public Enterprises
  • ንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ቅጂ/Copy of Business Registration Certificate,
  • የንግድ ፍቃድ ሰርተፊኬት ቅጂ/Copy of Business License Certificate,
  • የመጨረሻ/ዓመታዊ የሂሳብ መግለጫ/ Latest Annual Financial Report.
   • ኦዲት የተደረገ ከሆነ የኦዲት ድርጅቱ የሥራና የሙያ ፈቃድ ኮፒ አብሮ ይቀርባል፡፡
   • ኦዲት ያልተደረገና በውጭ ሂሳብ አዋቂ የተዘጋጀ ከሆነ የሂሳብ አዋቂ ድርጅቱ የሥራና የሙያ ፈቃድ ኮፒ አብሮ ይቀርባል፡፡
   • ኦዲት ያልተደረገና በውስጥ ሂሳብ ሠራተኛ የተዘጋጀ ከሆነ የሂሳብ ሠራተኛው የትምህርት ማስረጃና የፔሮል ኮፒ አብሮ ይቀርባል፡፡
  • የመቋቋሚያ አዋጅ ቅጂ/ copy of proclamation of establishment.

4.5     የሥራ አስኪያጅ 3×4 የሆነ ፎቶ ግራፍ/Manager’s 3×4 size photograph

 ሐ. ከዚህ በፊት የተመዘገቡና የሂሳብ መግለጫቸው በአለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት   ደረጃዎች (IFRS) ወይም የመካከለኛና አነስተኛ ድርጅቶች አለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ደረጃዎች (IFRS for SME) እና አለም አቀፍ የፐብሊክ ሴክተር የሂሳብ አያያዝ ደረጃዎች (IPSAS) ተግብረው የሂሳብ መግለጫቸው ለቦርዱ ለማስገባትና የማህተም አገልግሎት ለማግኘት መሟላት ያለባቸው ሰነዶች፤

 1. በትንሹ ሦስት ጥራዝ ኦርጂናል የሂሳብ መግለጫ/Minimum of Three Original Audit Report
 2. የኦዲት ድርጅቱ የሥራና ሙያ ፈቃድ ቅጂ/ Copy of the Audit Firm Business License and Professional Competency Certificate,
 3. ለ IFRS እና ለ IPSAS የሂሳብ ደረጃዎች ብር 685.00 (ስድስት መቶ ሰማንያ አምስት) እና ለIFRS for SME የሂሳብ ደረጃ ብር 540.00 (አምስት መቶ አርባ) በቦርዱ የሂሳብ ቁጥር 1000393097667 ገቢ ማድረግ
 4. የአገልግሎት ክፍያ ባንክ ገቢ የሆነበት የባንክ ደረሰኝ ቅጂ/ Copy of Service Fee Bank Deposit Slip,
 5. የሂሳብ ደረጃው ከGAAP ወደ IFRS የተቀየረው በውጭ ድርጅት ከሆነ ድርጅቱ ስምና ስልክ ቁጥር/ If the conversion has been completed by external body, Name and phone number of the firm or Consultant

 ማሳሰቢያ

የምዝገባው ቅጽ ሞልቶና ፈርሞ የሚያቀርበው ተወካይ ከሆነ የተወካይ በውልና ማስረጃ የተረጋገጠ ውክልና እና የታደሰ መታወቂያ ኮፒ ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡