ለሰራተኞች የደረጃዎች ትግበራ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡

የኢትዮጵያ የሒሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ ከሒሳብ አሰራር እና ኦዲት ሙያ ዉጪ ላሉ ለሁሉም ሰራተኞች በሁለት ፈረቃ ከታህሳስ 12 እስከ 15 2013ዓ.ም ከፍተኛ ጥራት ያላቸዉ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀት እና አቀራረብ ደረጃዎች (IFRS እና IPSAS) ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡

ስልጠናዉን የሰጡት የቦርዱ ባለሙያዎች አቶ ታዬ ፈቃዱ የሙያ እና የሙያ ማህበራት ክትትል ዳይሬክቶሬት ተ/ዳይሬክተር እና ወ/ሪት አለምገና ዘሪሁን የፋይናንስ ሪፖርት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሲሆኑ ስልጠናው ቦርዱ ለማከናወን ከተቋቋመባቸዉ ዓላማዎች አንዱ የሆነ የፋይናንስ ደረጃዎች ትግበራ ላይ አስፈላጊውን ግንዛቤ መጨበጥ ጠቀሜታዉ የጎላ መሆኑ ታምኖበት ነው፡፡

ሠራተኞችም የቦርዱ ራዕይ፣ተልዕኮና ዓላማን በመረዳት ለገፅታ ግንባታ ስራም እንደሚጠቅማቸዉ እንዲሁም ቦርዱ በሚያደርገዉ የ2013 በጀት ዓመት የዝግጅት ስራ አቅማቸውን በመገንባት ድርሻቸዉን እንደሚወጡ ለመረዳት ተችሏል፡፡