የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ጥሪ

Call for Sensitization workshop

 

በግልና በመንግስት ዘርፍ ባሉ ድርጅቶች ላይ ተፈጻሚ የሚሆን የተሟላ ግልጽና በቀላሉ ሊረዱት የሚችሉት የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ስረዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የፋይናንስ ሪፖርቶች በአለምአቀፍ የሪፖርት ደረጃዎች መሰረት እንዲዘጋጁና እንዲቀርቡ መንግስት የፋይናንስ ሪፖርት አዋጅ ቁጥር 847/2006 ማውጣቱ ይታወቃል፡፡ የሪፖርቶቹ  አዘገጃጀትና አቀራረብ በኃላፊነት እንዲመራና እንዲቆጣጠር በአዋጁ መሰረት  ለኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ስልጣን ተሰጥቷል፡፡

በዚሁ መሰረት ቦርዱ የትግበራ ፍኖተ-ካርታ አዘጋጅቶ ለሪፖርት አቅራቢ ድርጅቶች አዋጁን እና የአለምአቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ደረጃዎችን በተመለከተ ለመጀመሪያ ዙር ተግባሪዎች የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫና የስልጠና ወርክሾፖችን ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ቦርዱ በሁለተኛ ዙር ተግባሪዎች ከሆኑት ውስጥ የኢፌዴሪ በጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማህበራት ኤጀንሲ ተመዝግበው ፍቃድ ያደሱ የውጭ ሀገር በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት፣ የኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅቶች ፣የኢትዮጵያ ነዋሪዎች በጎ አድራጎት ድርጅቶች፣ብዙሀን ማህበራት እና የሙያ ማህበራት በሙሉ የአንድ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ወርክሾፖችን ያዘጋጀ በመሆኑ ከዚህ በታች በወጣው መርሃግብር መሰረት የመስሪያቤቶች፣ ዋና ኃላፊዎች (ስራ አስፈጻሚ)፣ የፋይናንስ ዋና ኃላፊዎች እና የኦዲት ኃላፊዎች የሆኑ ባጠቃላይ 3 ተሳታፊዎች በተጠቀሰው ቦታ እና ቀናት እንዲገኙልን እናስታውቃለን፡፡

ሀ.  የውጭ ሀገር የጎአድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት

ተ.ቁ  የደርጅቱ የምዝገባ ቁጥር ቀን ሰዓት ቦታ
1 1—3769 ሰኔ 2/ 2009 ከጠዋቱ 2፡30 አ.አ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፋኩልቲ አዳራሽ

ለ. የኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅቶች ፣የኢትዮጵያ ነዋሪዎች በጎ አድራጎት ድርጅቶች፣ብዙሀን ማህበራት እና የሙያ ማህበራት በሙሉ

ተ.ቁ  የደርጅቱ የምዝገባ ቁጥር ቀን ሰዓት ቦታ
2 1—453 ሰኔ 3/2009 ከጠዋቱ 2፡30 አ.አ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፋኩልቲ አዳራሽ
3 454—1168 ሰኔ 5/2009 ከጠዋቱ 2፡30 አ.አ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፋኩልቲ አዳራሽ
4 1169—1766 ሰኔ 6/2009 ከጠዋቱ 2፡30 አ.አ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፋኩልቲ አዳራሽ
5 1767—2335 ሰኔ 7/2009 ከጠዋቱ 2፡30 አ.አ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፋኩልቲ አዳራሽ
6 2336—2799 ሰኔ 8/2009 ከጠዋቱ 2፡30 አ.አ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፋኩልቲ አዳራሽ
7 2800—3268 ሰኔ 9/2009 ከጠዋቱ 2፡30 አ.አ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፋኩልቲ አዳራሽ
8 3269—3769 ሰኔ 10/2009 ከጠዋቱ 2፡30 አ.አ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፋኩልቲ አዳራሽ

 

ለበለጠ መረጃ፡

የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ድረ-ገጽ፡ www.aabe.gov.et

በስልክ ቁጥር +251 111 54 09 10፤+251-11 1 54 09 00፤+251 11 1 54 09 13  በመደወል ወይም

ስድስት ኪሎ ማዳጋስካር መንገድ  ሊደርሺፕ ህንጻ 4ኛ ፎቅ የሚገኘው የቦርዱ ቢሮ በአካል በመገኘት

በተጨማሪ፡ የኢፌዲሪ የበጎ አድራጎትና ማህበራት ኤጀንሲ (EFDR Charity and Society Agency) ድረ-ገጽ፡ www.chsa.gov.et እንዲሁም ግንቦት 27 ቀን 2009 ዓ/ም ከወጣው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ዝርዝር መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡