ለቦርዱ አገልግሎት ተጠቃሚዎች በሙሉ

 

የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ለተገልጋዮቹ ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 481/2013 በወጣው የአገልግሎት ክፍያ ታሪፍ መሰረት ክፍያ የሚያስፈፅም መሆኑ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ ተገልጋዮች ክፍያ የፈፀማችሁበትን ደረሰኝ ዋና (ኦሪጂናል) ይዛችሁ እንድትመጡ እያሳሰብን ቅጂ/ኮፒ ደረሰኝ ይዛችሁ የምትመጡ ደምበኞች ለአሰራር ስለምንቸግር በኮፒ የማናስተናግድ መሆኑን አውቃችሁ ክፍያ የተፈፀመበትን አሪጂናል ደረሰኝ ብቻ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡

ከሠላምታ ጋር

የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ