ለትርፍ ያልተቋቋሙ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የሂሳብ ሪፖርታቸውን የሚያዘጋጁበት የሂሳብ አያያዝ መመሪያ (INPAG) አስተዋወቀ

የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ከአለም አቀፍ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች የስራ ኃላፊዎች እና ፋይናንስ ባለሙያዎች ጋር ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች የፋይናንስ ሪፖርታቸውን የሚያዘጋጁበትን አዲስ መመሪያ (International Non-for Profit Accounting Guideline, INPAG) ን የማስተዋወቂያ ፕሮግራም  ሐሙስ ህዳር 01 ቀን 2015 ዓ.ም በዲ ሊኦፖል ሆቴል አካሄደ፡፡

በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቦርዱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሂክመት አብደላ ለትርፍ ላልተቋቋሙ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ለትርፍ ያልተቋቋመ የሂሳብ አያያዝ መመሪያ ወይም መስፈርት  (INPAG)  መጀመር እንዳለባቸው ለማስገንዘብ  መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በውይይቱ በመመሪያው የአተገባበር ተግዳሮቶች ላይ እና ከዓለምዓቀፍ የፐብሊክ ዘርፍ አካውንቲንግ ደረጃዎች/IPSAS ጋር ያለው አንድነትና ልዩነት እንዲሁም ከዚህ በፊት IPSASን የተገበሩ ተቋማት በቀላሉ መመሪያውን መተግበር እንደሚችሉ የተገለጸ ሲሆን IPSAS ላልተገበሩትም ቢሆን አዲሱ የሂሳብ አዘገጃጀት መመሪያ ለሁሉም በሚመች መልኩ መዘጋጀቱ ተመላክቷል፡፡

በመጨረሻም አዲሱን መመሪያ በሀገራችን በ2025 (እ.ኤ.አ) ለመተግበር የተያዘውን እቅድ ለማሳካት ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ከተቆጣጣሪ አካላት ጋርም የጋራ እቅድ በማውጣት በቅንጅት መሰራት እንዳለበት ተጠቅሷል፡፡