የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ በአዎጅ ቁጥር 847/2006 አንቀፅ 4 (2)(መ) የሪፖርት አቅራቢ አካላትን የህዝብ ጥቅም ያለባቸው ወይም አነስተኛና መካከለኛ በሚል መለየት የሚያስችል መስፈርቶችን በማውጣት እነዲመዘግብ ስልጣን የተሰጠው መሆኑ ይታወቃል፡፡
እንዲሁም ደግሞ በአንቀፅ 8 (1) እና 4(2)(ሸ) ማንኛውም ሪፖርት አቅራቢ አካል ቦርዱ በሚያወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የሂሳብ መግለጫውን ለቦርዱ ማቅረብ እንዳለበት፤ ቦርዱ አነዚህን ሪፖርቶች የመገምገምና ፍላጎት ላላቸው ባለድርሻ አካላት ተደራሽ የሚሆኑበትን ሁኔታ እንዲያመቻች ተደንግጓል፡፡
በዚሁ መሠረት ቦርዱ የሪፖርት አቅራቢ አካላት ከነባሩ አሰራር ወደ አለምአቀፍ ደረጃዎች የሚደርጉነትን ሽግግር በተሳካ ሁኔታ ለማስተግበር የትግበራ ፍኖተ-ካርታ አዘጋጅቶ ሪፖርት አቅራቢ ድርጅቶችን ለመመዝገብ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡
በመሆኑም በኢ.ፌ.ድ.ሪ የገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን የታክስ አከፋፈል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤታችሁ መሰረት በአዲስ አበባ የምትገኙ ግብር ከፋዮች የሆናችሁ እና የ2008 ዓ.ም አጠቃላይ አመታዊ ሽያጫችሁ ከአንድ ሚሊዮን(1,000,000)ብር በላይ የሆነ ወይም ድርጅት/ኩባንያዎች(Share companies and private limited companies)የሆናችሁ በሙሉ፡፡ከዚህ ቀጥሎ በወጣላችሁ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ በአካል በመገኘት ድርጅታችሁን እንድታስመዘግቡ እናስታውቃለን፡፡
የምዝገባ የጊዜ ሰሌዳ
ተ.ቁ | የገቢዎች ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት | የምዝገባ ቀናት | የምዝገባ ቦታ |
1 | ልደታ |
ከሰኔ 15/2009 እስከ ሀምሌ 28/20 09ዓ.ም ባሉት የስራ ቀናት
|
የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ፣ስድስት ኪሎ ማዳጋስካር መንገድ ሊደርሺፕ ህንጻ 4ኛ ፎቅ
|
2 | አቃቂ ቃሊቲ | ||
3 | አዲስ ከተማ | ||
4 | አራዳ | ||
5 | መርካቶ ቁጥር አንድ |
ከነሐሴ1/2009 ዓ.ም እስከ መስከረም 30/2010ዓ.ም ባሉት የስራ ቀናት የስራ ቀናት
|
የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ፣ስድስት ኪሎ ማዳጋስካር መንገድ ሊደርሺፕ ህንጻ 4ኛ ፎቅ
|
6 | መርካቶ ቁጥር ሁለት | ||
7 | ጉለሌ | ||
8 | ቂርቆስ | ||
9 | አዲስ አበባ ቁጥር 1 |
ከጥቅምት01 /2010ዓ.ም አስከ ህዳር 29 /2010ዓ.ም ባሉት የስራ ቀናት |
የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ፣ስድስት ኪሎ ማዳጋስካር መንገድ ሊደርሺፕ ህንጻ 4ኛ ፎቅ
|
10 | አዲስ አበባ ቁጥር 2 | ||
11 | የካ | ||
12 | ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ | ||
13 | ቦሌ |
ከታህሳስ 02/2010ዓ.ም እስከ ታህሳስ 30/2010ዓ.ም ባሉት የስራ ቀናት |
የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ፣ስድስት ኪሎ ማዳጋስካር መንገድ ሊደርሺፕ ህንጻ 4ኛ ፎቅ |
14 | ኮ/ቀ/ክ/ከተማ | ||
15 |
ምዕራብ አዲስ አበባ |
||
16 |
ምስራቅ አዲስ አበባ |
ለከፍተኛ ግብር ከፋዮች በሙሉ
የምዝገባ የጊዜ ሰሌዳ
ተመዝጋቢዎች– -ከፍተኛ ግብር ከፋዮች
የምዝገባ ቀናት – ከሰኔ 22/2009 እስከ ሀምሌ 28/2009ዓ.ም ባሉት የስራ ቀናት
በስልክ ቁጥር +251 111 54 09 10፤+251-11 1 54 09 00፤+251 11 1 54 09 13 በመደወል ወይም
ስድስት ኪሎ ማዳጋስካር መንገድ ሊደርሺፕ ህንጻ 4ኛ ፎቅ የሚገኘው የቦርዱ ቢሮ በአካል በመገኘት
Leave A Comment
You must be logged in to post a comment.