ለኦዲት ባለሙያዎች የደረጃዎች ትግበራ ስልጠና ተሰጠ፡፡
የካቲት 28 ቀን 2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ፤
የኢትዮጵያ የሒሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ” ISQM1, ISA 315 and ISA 240“ዓለም-አቀፍ የኦዲት ሪፖርት ስታንዳርድን አስመልክቶ ለኦዲት ድርጅቶች በበይነ-መረብ ለሶስት ቀናት በኢንተርሌግዠሪ ሆቴል ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል፡፡
ስልጠናው የኦዲት ባህል ግምገማን መሰረት ያደረገ በመሆኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ የወጡ አዳዲስ ስታንዳርዶችን ለመተግበር የሚያስችል መሆኑን ተሳታፊዎች ገልጸዋል፡፡
የኦዲት ድርጅቶች በስልጠና ቆይታቸው” ISQM1, ISA 315 and ISA 240“ስታንዳርዶችን ለመተግበር አቅም እንደተፈጠረላቸው ገልጸው በዚህም ጥራት ያለው የኦዲት ሪፖርት እንዲወጣ ሁሉም የኦዲት ባለሙያ የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡
የኦዲት ሪፖርት ጥራትን ለማስጠበቅ እንደ ሀገር ብቁ የሆነ ባለሙያ በበቂ ሁኔታ ሊኖር እንደሚገባ እንዲሁም መሰል የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ አስተያየታቸውን የሰጡን የኦዲት ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡
የባለሙያ እጥረት ችግርን ለመፍታት በሀገር ውስጥ ኢንስቲትዩት እንዲቋቋም በሚመለከታቸው አካላት እየተሰራ መሆኑን ገልጸው የኦዲት ድርጅቶች ጥራት ያለው የኦዲት ሪፖርት በማውጣት ሙያዊ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የቦርዱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ አጎናፍር አሳስበዋል፡፡