የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ጥሪ
Call for Sensitization workshop
መንግስት በግልና በመንግስት ዘርፍ ባሉ ድርጅቶች ላይ ተፈፃሚ የሚሆን የተሟላ ግልጽና በቀላሉ ሊረዱት የሚችሉት የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኙቱ የፋይናንስ ሪፖርቶች በአለምአቀፍ የሪፖርት ደረጃዎች መሠረት እንዲዘጋጁና እንዲቀርቡ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ አዋጅ ቁጥር 847/2ዐዐ6 ማውጣቱ ይታወቃል፡፡አዋጁን በሚገባ ለማስፈጸም እንዲቻል የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ በሚኒስተሮች ምክርቤት ቁጥር 332/2007 ተቋቁሞ ለትግበራው እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
በዚሁ መሰረት ቦርዱ የትግበራ ፍኖተ-ካርታ አዘጋጅቶ ለሪፖርት አቅራቢ ድርጅቶች አዋጁን እና የአለምአቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ደረጃዎችን በተመለከተ ለመጀመሪያ ዙር ተግባሪዎች የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫና የስልጠና ወርክሾፖችን ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ቦርዱ በሁለተኛ ዙር ተግባሪዎች ከሆኑት ውስጥ ለከፍተኛ ግብር ከፋዮች በሙሉ የአንድ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ወርክሾፕ ሰኔ 13 ቀን 2009 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 በአ.አ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፋኩልቲ አዳራሽ ያዘጋጀ በመሆኑ የመስሪያቤቶች፣ ዋና ኃላፊዎች (ስራ አስፈጻሚ)፣ የፋይናንስ ዋና ኃላፊዎች እና የኦዲት ኃላፊዎች የሆኑ ባጠቃላይ 3 ተሳታፊዎች በተጠቀሰው ቦታ እና ቀናት እንዲገኙልን እናስታውቃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ፡
በስልክ ቁጥር +251-11 1 54 09 00፤+251 11 1 54 09 13 በመደወል ወይም
ስድስት ኪሎ ማዳጋስካር መንገድ ሊደርሺፕ ህንጻ 4ኛ ፎቅ የሚገኘው የቦርዱ ቢሮ በአካል በመገኘት
Leave A Comment
You must be logged in to post a comment.