ለደቡብ እና ለሲዳማ ክልል የሒሳብ እና ኦዲት ባለሙያዎች የሙያ ፍቃድ እድሳት በቦርዱ በኩል እንደሚከናወን ተገለፀ፡፡

የኢትዮጵያ የሒሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ በደቡብ ክልል እና በሲዳማ ክልል ለሚገኙ 139 የሒሳብ እና ኦዲት ባለሙያዎች የሒሳብ እና ኦዲት ሙያ ፍቃድ በቦርዱ በኩል እንደሚከናወን ነሐሴ 04 ቀን 2014 ዓ.ም በሐዋሳ ከተማ ከባለሙያዎቹ ጋር በተደረገው የውይይት መድረክ አስታወቀ፡፡

በዕለቱም የቦርዱ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳ/ት ዳ/ር አቶ አበበ ሺፈራው ለባለሙያዎቹ የእን£ን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን ባስተላለፉበት ወቅት ለቦርዱ መssም መነሻ የሆኑ ጉዳዮችን በማውሳት በህግ የተሰጡትን ኃላፊነትና ተግባራት አብራርተዋል፡፡

ቦርዱ በኢትዮጵያ የሒሳብ አያያዝ ሙያን የማስተባበር እና የመቆጣጠር ኃላፊነት የተሰጠው ተsም መሆኑን አስረድተው ቀድሞ ክልሎች በጊዜያዊነት ሙያውን እንዲያስተባብሩ የገንዘብ ሚኒስቴር ሰጥቶ የነበረውን ውክልና ከየካቲት 16 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ያነሳ እና ሙያው በሀገር ዓቀፍ ደረጃ ወጥነት እንዲኖረው የባለሙያዎቹ ፍቃድ በቦርዱ በኩል መታደስ እና ተገቢው ክትትልና ድጋፍም ሊደረግ እንደሚገባ በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት ሲሆን የሙያ ፍቃዱ የሚታደስላቸው በሁለቱም ክልሎች ዋና ኦዲተሮች ወደ ቦርዱ የተላኩ የ139 ባለሙያዎች ፍቃድ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የሙያ ትምህርት እና ብቃት ማረጋገጫ ፈተናዎች ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ አቶ ደገፋ በንቲ የሙያ ፍቃድ እድሳቱ በሚከናወንበት ወቅት ባለሙያዎቹ ማሟላት ስለሚገቧቸው ቅድመ-ሁኔታዎች እና መስፈርቶችን ያብራሩ ሲሆን የቦርዱ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዳ/ት ዳ/ር አቶ ተከታይ ደለለኝ እድሳቱ በኤሌክተሮኒክ የአገልግሎት አሰጣጥ ዘዴ (https://www.eservices.gov.et/provider/1021) በኩል እንደሚከናወን በማስረዳት ለባለሙያዎቹ ተግባራዊ ልምምዶችም አድርገውላቸዋል፡፡

በተካሄደው ውይይትም ሙያው ዓለም-ዓቀፍ ደረጃውን በጠበቀ የፋይናንስ ሪፖርት የማዘጋጀት እና የማቅረብ አቅም ባለው ባለሙያ መከናወን ያለበት እና ባለሀብቶችን/ኢንቬስተሮችን ለመሳብ ተወዳዳሪነትን የሚያበረታታ እንደመሆኑ መጠን ለባለሙያው ሊደረጉ ስለሚገቡ የተደራሽነት/የቅርብ ክትትሎች፣ ድጋፎች እና የአቅም ግንባታ ጉዳዮች፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር መሰራት ስለሚገቧቸው ተግባራት፣ ህገ-ወጥ የሙያ ተግባራትን መከላከል እና ህግን በሚጥሱት ላይ መወሰድ ስለሚገቡ እርምጃዎች፣ የኢንስቲትዩት ማssም ሂደትም በሚመለታቸው አካላት ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ እና ሌሎችም አስተያየቶች እና ጥያቄዎች ተነስተው ሰፋ ያለ ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘም በሐዋሳ ከተማ በሚገኙ 14 የሂሳብ እና የኦዲት ሙያ ድርጅቶች ላይ የመስክ ምልከታ ተደርጓል፡፡