በክልሎች ይሰጡ የነበሩ የሒሳብ ሙያ ፍቀድና አድሳት አገልግሎቶች ወደ ቦርዱ እየመጡ ነው

የደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ዋና ኦዲተር በገንዘብ ሚኒስቴር በተሰጠው ውክልና መሰረት ሲሰጥ የነበረውን የሂሳብና የኦዲት ሙያ ፈቃድ እና እድሳት አገልግሎት ከየካቲት 16 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ሚኒስትር መስሪያቤቱ ውክልናውን በማንሳቱ በኢትዮጵያ የሒሳብ ሙያን (Accountancy Profession) እንዲቆጣጠር በአዋጅ ኃላፊነት እና ሥልጣን ለተሰጠው ለኢትዮጵያ የሒሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ የ135(አንድመቶ ሠላሳ አምስት) ግለሰቦች ሰነዶች በመስሪያ ቤቱ ተወካይ ወ/ሮ መክሊት ከበደ አስረክቧል፡፡

የቦርዱ የሙያ ትምህርትና የብቃት ማረጋገጫ ፈተናዎች ዳይሬክቶሬት ተ/ዳይሬክተር አቶ ረታ አበበ እንደገለጹት ቦርዱ ከተቋቋመበት ዓላማ አንዱ በኢትዮጵያ የሂሳብና የኦዲት ሙያ ፈቃድ እና እድሳት አገልግሎት በአገር አቀፍ ደረጃ ወጥነት እንዲኖረውና ባለሙያዎቸም ለሙያው ተቀባይነት ያላቸውን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆናቸውን ማረጋገጥ አንዱ ነው ብለዋል፡፡

በዕለቱ ቦርዱ ከተረከባቸው ሰነዶች መካከል 132(አንድ መቶ ሠላሳ ሁለት) የሂሳብ ሙያ ፍቃድ ሲሆን ቀረዎቹ 3(ሦስት) የኦዲት ሙያ ፍቃድ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ 27(ሃያ ሰባት) የሐረሪ ክልል ሙያተኞች ባለፈው ሰኔ 2014 ዓ.ም. ሙሉ ሰነዶቻቸውን ለቦርዱ ማስረከባቸውን ተከትሎ የ2015 ዓ.ም. የሙያ ፍቃድ እድሳት እያከናወኑ ይገኛል፡፡