ቦርዱ ለሂሳብና ኦዲት ባለሙያዎቹ   በሁለት ዙር የአቅም ግንባታ ሰልጠና ተሰጠ::

የኢትዮጵያ   የሂሳብ አያያዝና   ኦዲት ቦርድ  ከህዳር  21 እስከ  ታህሳስ 2/2013 ዓ.ም በሁለት ዙር የአቅም ግንባታ ስልጠና ለቦርዱ  የሂሳብና ኦዲት ባለሙያዎቹ በአዲስ አበባ  ራስ  አምባ  ሆቴል የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ።በስልጠናውም ከሁሉም  የቦርዱ  ዋና  የስራ ሂደቶች የሂሳብና ኦዲት ባለሙያዎች  እንዲሁም  ከደጋፊ የስራ ሂደቶች ከፋይናንስ እና  ኦዲት ዳይሬክቶሬት ለተውጣጡ  ባለሙያዎች  በድምሩ ለ23 የቦርዱ  ሰራተኞች የአቅም ግንባታ ስልጠናን ሰጥቷል ።

የስልጠናው አስተባባሪ በቦርዱ የኦዲት ማረጋገጥ ደረጃዎች  ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቃኘው እሸቴ እንደገለፁት “የስልጠናው  አላማ የቦርዱን  የቀጣይ አምስት አመታት ስትራቴጂክ እቅድ ለማሳካት በቀዳሚነት የባለሙያዎችን የውስጥ አቅም ስራው  በሚፈልገው ሙያዊ እውቀት እና  ክህሎት በማሰልጠን ማብቃት አስፈላጊ  መሆኑ እና አቅሙ የተገነባ የቦርዱ ባለሙያም የተሻለ አገልግሎት መስጠት እንደሚችል ቦርዱ  ስለሚያምን ስልጠናውን አዘጋጅቷል።” ብለዋል።

ስልጠናውን እየሰጡ ያሉት በቦርዱ የሙያና የሙያ ማህበራት ቁጥጥርና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታዬ ፈቃዱ “በስልጠናው የተካተቱት  ይዘቶች  የኦዲት ደረጃዎች፣አለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፓርት ደረጃዎች እና አለም አቀፍ የፐብሊክ ሴክተር  የሂሳብ ደረጃዎች  (IPSAS)   መሆናቸውን ገልፀው ቦርዱ በዋነኛነት ለሚከውናቸው የተግባር ተኮር የሂሳብና  ኦዲት ሪፓርት ምልከታ (Practical Review)አገልግሎት  አሰጣጥ ውጤታማነት አለም  አቀፍ እውቅና ካለው የተመሰከረላቸው  የሂሳብና ኦዲት ባለሙያዎች  ማህበር (ACCA)ለቦርዱ ሰራተኞች ተግባር ተኮር የሂሳብና ኦዲት  ስልጠና ያግዝ ዘንድ ግንዛቤን ለመፍጠር ስልጠናው ማዘጋጀቱን ገልፀው፤ሰልጣኝ የቦርዱ ባለሙያዎች ለሚሰጡት አገልግሎት እና በኢትዮጵያ ከፍተኛ ጥራት ያልው የፋይናንስ ሪፖርት አዝገጃጀትና አቀራረብ ደረጃዎች ትግበራን አውን ለማድርግ ያለው ሚና ወሳኝ ነው “ብለዋል።