የሕግ ጥሰት የፈጸመ የሒሳብ ባለሙያ ቅጣት ተጣለበት፡፡

የካቲት 21 ቀን 2016ዓ/ም

የኢትዮጵያ የሒሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ

በኢትዮጵያ የሒሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ የሂሳብ ሙያ ህጋዊ ፈቃድ ወስዶ ከሙያ ሥነ-ምግባር ውጭ የሕግ ጥሰት ሲፈጽም የተገኘ የሂሳብ ባለሙያ በገንዘብ መቀጣቱ ተገለጸ፡፡

በቦርዱ የሕግ ማስከበር መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወርቁ አዲስ እንደገለጹት በሒሳብ እና ኦዲት ሙያ ላይ የሚያጋጥሙ ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴዎችን ለመከላከል በሚደረግ የክትትል እና ቁጥጥር ሥራ ከቦርዱ ህጋዊ ፈቃድ ወስዶ የሕግ ጥሰት ሲፈጽም በተገኘ የሒሳብ ባለሙያ ምርመራ ተጣርቶ በቦርዱ ክስ ሰሚ ችሎት በቀረበበት ክስ መሰረት በመመመሪያው መሰረት ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በገንዘብ መቀጣቱን ገልጸዋል፡፡

ጥራት ያለው የፋይናንስ ሪፖርት በማዘጋጀት የሕዝብ ጥቅምን ለማስጠበቅ በሒሳብ እና ኦዲት ሙያ ላይ ሕገ-ወጥነትን በመከላከል ረገድ በሚሰሩ ሥራዎች ሁሉም ባለድርሻ አካል የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባም መሪ ሥራ አስፈጻሚው አሳስበዋል፡፡