የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ የአገልግሎት ክፍያ ደን ፀደቀ

የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ የሂሳብ እና ኦዲት ሙያ አገልግሎት ጥራትን በማሳደግ ሙያው የህዝብ ጥቅምን ማስጠበቁን ለማረጋገጥ ያሉ የህግ ማዕቀፎችን ተግባራዊ ማድረግ እና አዳዲስ ህጎችንም በማዘጋጀት ስራ ላይ እንዲውሉ እያደረገ ይገኛል፡፡

በዚሁ መሰረት በቦርዱ ተዘጋጅቶ የቀረበው የአገልግሎት ክፍያ ረቂቅ ደንብ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸድቋል፡፡

ደንቡ በሪፖርት አቅራቢ አካላት (ከፍተኛ የህዝብ ጥቅም ያለባቸው እና አነስተኛ ወይም መካከለኛ ድርጅቶች) ፣ የሂሳብ እና ኦዲት ባለሙያዎች እና ድርጅቶች፣ በሙያ ማህበራት እና የፋይናንስ ሪፖርት መረጃ ፈላጊዎች (አጥኚዎችን ሳይጨምር) ላይ ተግባራዊ የሚሆን ነው፡፡

የአገልግሎት ክፍያ ተመኑን በጥናት አስደግፎ ማዘጋጀት ያስፈለገው ቦርዱ ለተገልጋዮች ቀልጣፋና ውጤታማ የሆነ አገልግሎት መስጠት እንዲያስችለው በዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል በመመደብ፣ ቋሚና ቋሚ-ያልሆኑ ንብረቶችን በማቅረብ እና ሌሎች ግብዓቶችን በማሟላት ረገድ የሚያወጣቸው ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ ወጪዎችን ለመሸፈን በማስፈለጉ ነው፡፡