እንኳን አደረሳችሁ

የግል የሒሳብ ሙያ ፈቃድ በእጃቸሁ ላለ ግለሰቦች በሙሉ

የኢትዮጵያ የሒሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ ለሒሳብ እና ኦዲት ባለሙያዎች የሙያ ፈቃድ አሰጣጥ እና የሒሳብ ሙያ ማህበራት ምዝገባ መመሪያ ቁጥር 805/2013 መሰረት በእጃቸው የግል የሒሳብ/ኦዲት የሙያ ፍቃድ የምስክር ወረቀት የያዙ ባለሙያዎች ፍቃዱ በተሰጣቸው በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ የምስክር ወረቀቱን (Competency Certificate) መልሰው የሂሳብ/ኦዲት ሙያ አገልግሎት መስጠት የሚያስችላቸውን ድርጅት መክፈት እንዳለባቸው ያስገድዳል፡፡

በርካታ ባለሙያዎችም የግል የሙያ ፍቃዳቸውን ወደ ድርጅት እየቀየሩ ቢሆንም የተቀመጠው የጊዜ ገደብ በማለቁ እና በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ምክንያት የተወሰኑት እንዲራዘምላቸው በጠየቁት መሰረት ቦርዱ ጊዜውን ማራዘሙን ያሳውቃል፡፡

በዚሁ መሰረት የግል የሂሳብ ሙያ ፍቃድ በእጃችሁ የያዛችሁ ግለሰቦች እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ወደ ሒሳብ ሙያ ድርጅት እንድትቀይሩ ወይም እንድትመልሱ እንዲሁም የምስክር ወረቀቱ ከተጠቀሰው ቀን በኋላ ህጋዊነት የሌለው እና መመሪያውን በማያከብሩት ላይ ቦርዱ አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑን በማሳሰብ ከወዲሁ ሙያዊ ግዴታችሁን እንድትወጡ ያሳውቃል፡፡

                              የኢትዮጵያ የሒሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ

መልካም በዓል ይሁንላችሁ