ከክልል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የሒሳብ እና የኦዲት ፈቃድ ለተሰጣችሁ ባለሙያዎች

ማስታወቂያ ከክልል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የሒሳብ እና የኦዲት ፈቃድ ለተሰጣችሁ ባለሙያዎች ለሒሳብ እና ኦዲት ባለሙያዎች ፈቃድ የመስጠት፣ የማደስ እና የመቆጣጠር ሥልጣን ለክልል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በውክልና ተሰጥቶ የነበረ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን ከየካቲት 16 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ ውክልናው የተነሳ በመሆኑ ፍቃድ የመስጠት፣ የማደስ እና ባለሙያዎችን የመቆጣጠር ተግባር በኢትዮጵያ የሒሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ እየተከናወነ ይገኛል፡፡ [...]