የችግኝ ተከላ በአዋዬ ቀበሌ ተካሄደ

የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ከገንዘብ ሚነስቴር እና ተጠሪ ተቋማቱ ጋር በደቡብ ክልል ከንባታ ጠንባሮ ዞን ቃጫ ቢራ ወረዳ አዋዬ ቀበሌ ሐምሌ 9 ቀን 2014ዓ.ም የችግኝ ተከላ እና የአቅመ ደካሞችን መኖሪያ ቤት እድሳት አከናወነ፡፡

መርሃ-ግብሩን የመሩት የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር የሆኑት አቶ አህመድ ሽዴ እንደተናገሩት የደን መመናመን ለዓለም ከባቢ አየር ለውጥ ምክንያት ከመሆኑም አልፎ ዜጎችን ለረሃብ በማጋለጥ ላይ እንደሚገኝ ጠቁመው ሀገራችን ለ4ኛ ጊዜ በተከታይነት ችግሩን ለመቅረፍ በምታደርገው ትግል አሻራችንን ማኖር አለብን ብለዋል፡፡

በዕለቱም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው እና የተጠሪ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች አሻራቸውን አሳርፈዋል፤ በሺንሺቾ ከተማ የሚገኙ የአቅመ ደካሞችን የመኖሪያ ቤት ዕድሳት ሥራም አስጀምረዋል፡፡