ቀን፡- 02/03/2015ዓ.ም.                              

ማስታወቂያ           

ለሙያዊ አጋርነት የቀረበ ጥሪ

የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ በህግ የተሰጡትን ኃላፊነትና ተግባራት ለመወጣት ባለፉት ጥቂት አመታት በርካታ ተግባራትን አከናውኗል፣ በማከናወንም ላይ ይገኛል፡፡

በዚሁም መሠረት ቦርዱ በዳይሬክተሮች ቦርድ የሚመራ ሲሆን የአስር ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ (2013-2022) በማዘጋጀት ወደ ተግባር የገባ ከመሆኑም በተጨማሪ የዳይሬክቶሬቶች ቦርድ አመራር አባላቱም ለዕቅዱ ስኬታማነት በሦስት ንዑሳን ኮሚቴዎች ማለትም፡-

  1. Strategy & corporate governance committee,
  2. Practice review, investigation and monitoring committee &
  3. Financial reporting and Auditing standards committee ተዋቅረው ወደ ውጤታማ ስራ ገብተዋል፡፡

በመሆኑም ቦርዱ ከላይ በተዘረዘሩት ንዑሳን ኮሚቴዎች ውስጥ በሙያቸው ለማገዝ እና በአጋርነት ለማገልገል የሚፈልጉ ባለሙያዎችን በበጎ ፍቃደኝነት መልምሎ በመመደብ አብሮ ለመስራት ይፈልጋል፡፡

 

ስለሆነም በሙያው (Accountancy) ውስጥ ያላችሁ እና ቢያንስ ሲፒኤ የሆናችሁ በበጎ ፍቃደኝነት ለማገልገል የምትፈልጉ አካላት ከላይ ከተዘረዘሩ ንዑሳን ኮሚቴዎች ውስጥ ምርጫችሁን በመጥቀስ እስከ ህዳር 30/2015 ዓ.ም ድረስ ያሏችሁን ደጋፊ መረጃዎች (CV & CPA) በማቅረብ በቦርዱ ኢሜይል infoaabe20@gmail.com በኩል በመመዝገብ አጋርነታችሁን እንድታሳውቁን ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ለበለጠ መረጃ፡-    በስልክ ቁ.  0111540900 ወይም ከላይ በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ መጠቀም ይቻላል፡፡

                       የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ