10/05/2015 ዓ.ም

ለሒሳብ እና ለኦዲት ሙያ ድርጅት ባለቤቶች በሙሉ

ጉዳዩ፡ የአገልግሎት ክፍያን ይመለከታል

የኢትዮጵያ የሒሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ለጥምቀት በዓል በሠላም አደረሳችሁ እያለ በደንብ ቁጥር 481/2013 መሠረት ቦርዱ ለሚሰጣቸዉ አገልግሎቶች ክፍያን እንደሚያስከፍል ይደነግጋል።

በዚህም መሠረት የሒሳብ ወይም የኦዲት ሙያ ድርጅት ባለቤቶች የ2015/16 በጀት ዓመት የሙያ ፈቃድ ምስክር ወረቀት ዕድሳት የአገልግሎት ክፍያችሁን በመመሪያዉ መሠረት በቴሌብር በመክፈል እንድታሳድሱ እየጠየቅን፤

ከዚህ በፊት የግል የሒሳብ/የኦዲት (Individual Certificate) ሙያ ፈቃድ  የምስክር ወረቀት ለ2014 ለማሳደስ የአገልግሎት ክፍያ የከፈላችሁና አገልግሎቱን ያገኛችሁ በሙሉ የ2015/16 በጀት ዓመት የሙያ ምዝገባ ፈቃድ ምስክር ወረቀት ዕድሳት የአገልግሎት ክፍያዉ የሚመለከታችሁ ስለሆነ የምትከፍሉ መሆኑን እያሳወቅን ሆኖም ግን ለ2014 ለግል የሒሳብ/የኦዲት የምስክር ወረቀት (Individual Certificate) ከፍላችሁ አገልግሎቱን ያላገኛችሁ ማለትም ሁለት ጊዜ ክፍያ ፈጽማችሁ የግሉን ያላሳደሳችሁ መረጀዉን አያይዛችሁ ስታቀረቡ የምናሰተናግድ መሆኑን እንገልጻልን።

 

ማሳሰብያ፡- የሒሳብ ወይም የኦዲት ሙያ የምዝገባ ምስክር ወረቀት እድሳት እስከ ጥር 30/2015 ብቻ የሚቆይ መሆኑን አዉቃችሁ አላስፈላጊ ቅጣት ዉስጥ ከመግባት ከወዲሁ አስፈላጊዉን መሥፈርት በማሟላት ፎርሙን በኢሰርቪሱ ብቻ ሞልታቸዉ እንዲታሳድሱ እናሳስባለን።

በተጨማሪም የአገልግሎት ክፍያን እንዴት እንደምትከፍሉ የሚያሳይ ቪዲዮ በቦርዱ የዩቲውብ አድራሻ ( https://www.youtube.com/@accountingandauditingboard9926 ) በዚህ ሊንክ በመግባት ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

የኢትዮጵያ የሒሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ