በቦርዱ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያዎች እና የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ደረጃዎች /IFRS/ ሥርዓት ትግበራ ዙሪያ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ እና በሥሩ ካሉ ተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ጋር መክሮ ቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቀቀ፡፡
============================================
ሚያዝያ 22 ቀን 2015 ዓ.ም.
አዳማ
የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ የተቋቋመበት አዋጅ፣ ደንብና መመሪያዎች እንዲሁም የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ደረጃዎች/IFRS/ሥርዓት አተገባበር ዙሪያ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ሚያዝያ 21 ቀን 2015 ዓ.ም. በአዳማ ኤግዚኪዩቲቭ ሆቴል ባካሄደው የምክክር መድረክ ቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ አጠናቋል፡፡
በምክክሩ ላይ የተገኙት አቶ ፍቃዱ አጎናፍር የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ባስተላለፉት መልዕክት ተሳታፊዎችን የእንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ በኋላ “በኢትዮጵያ የፋይናንስ አስተዳደር ሥርዓትን ለማጎለበት በኢትዮጵያ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ደረጃዎች/IFRS/ሥርዓት ለማስተግበር ሥልጣን የተሰጠው ለቦርዱ እንደመሆኑ የፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብ ደረጃዎች /IFRS/ ሥርዓትን ጠቀሜታ ኅብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲኖረው በማድረግ በተለይ እነማን ናቸው አሠራሩን የሚተገብሩት የሚሉትን ግልጽ እንዲሆን ላለፉት ዓመታት የተለያዩ የማስተዋወቂያ ሥራዎች ሲሠራበት” መቆየቱን በማስገንዘብ መድረኩን አስጀምረዋል፡፡
በምክክሩ መርሐግብር መሰረት በቦርዱ ማቋቋሚያ አዋጅ ደንብና መመሪያዎች ዙሪያ በተለያየ ደረጃ ላሉ ባለድርሻ አካላት ሲያስተዋውቅ መቆየቱን በተለይ በሪፖርት አቅራቢ አካላት እና የባለሙያዎች በሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ደረጃዎች ሊኖር በሚገባው ሥነ ምግባርን አስመልክቶ በአቶ ወርቁ አዲስ በቦርዱ የሕግ ማስከበር መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሰፊ ገለፃ ተደርጓል፡፡
ኃላፊው በገለፃቸው የሕዝብ ጥቅም ያለባቸው ተቋማት ወደ ቦርዱ መጥተው መመዝገብ እንዳለባቸውና እስከ 2015 በጀት ዓመት ማጠናቀቂያ ድረስ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀት፣ አቀራረብ ደረጃዎች /IFRS/ ስርዓት ሙሉ ትግበራ (Full implementation) በማድረግ ወጥ ሪፖርቶችን እንደሚያቀርቡ እንዲሁም አነስተኛና መካከለኛ የበጎ አድራጎት እና ማህበራት የሆኑት ከ2016ዓ.ም ጀምሮ የሚተገብሩ መሆኑን መረጃ በመስጠት ካብራሩ በኋላ ተሳታፊዎች አስተያየትና ጥንቄ በማንሳት ፍሬያማ ውይይቶች ተደርጎባቸዋል፡፡
ከነዚህም መካከል ከታክስ አስተዳደር ሥርዓት ጋር በተያያዘም ትልልቅ ባለሀብቶች፣ መካከለኛ ባለሀብቶች፣ አነስተኛ ባለሀብቶች፣ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ደረጃዎች/IFRS/ሥርዓትን በመለማመድ ወደ ሙሉ ትግበራ እንዲገቡ ለማስቻል በርካታ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች በኋላ ከየተቋመቱ የቀረቡልንን የሂሳብ መግለጫ ሪፖርቶችን በመገምገም ያገኘው ውጤት በርካታ ክፍተቶች ያሉበትና እስካሁንም በሚፈለገው ደረጃ ያልደረሰ መሆኑን መመላከቱን፣
በተለይ ለገቢ ግብር ዓላማ ከግብር ከፋይ የሚቀርቡ የሂሳብ መግለጫ ሪፖርቶች ከፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ደረጃዎች/IFRS/ሥርዓት ጋር ሲታይ ወጥነት የሚጎለው በመሆኑ በተገቢው መንገድ የመደጋገፍ አሠራር ስርዓት በማበጀት መስመር የማስያዝ ሥራ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ፣ የሚቀርቡ የሂሳብ መግለጫዎች ትክክለኛነት ከሂሳብ መዝገቦች ጋር ለማመሳከር እንዲቻል የበቁ የሂሳብ ባለሙያዎች በገበያ ላይ የማፍራት ሥራ በትምህርት ተቋማት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማሳሰብ እንደሚገባ ከውይይቱ ተሳታፊዎች የተንሸራሸሩ ነጥቦች ናቸው፡፡
በሌላ በኩል ከታክስ ስርዓቱ በአንድአንድ ሊከሰቱ በሚችሉ የህግ ጥሰቶችን፣ ሕገ-ወጥነትን፣ የፎርጀሪ ስራዎችን ለመከላከል እንዲቻል በጋራ የመስራት ባህልን ማዳበር እንደሚገባ፣ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀት፣ አቀራረብ ደረጃዎችን ለማስጠበቅ የሂሳብ መግለጫዎች አጥጋቢነትና ትክክለኛነት የማረጋገጥ፣ እንዲሁም ለካፒታል ኢንቨስትመንት ብድር ማግኛ የሚቀርቡ የሂሳብ መግለጫዎች ከ”IFRS”ሥርዓት የሪፖርት አቀራረብ ጋር ሲታይ የወጥነት ችግሮች ያሉበት መሆኑ በግማገማ (ፋይናሺያል ሪቪው) በተገኘው ውጤት ስለመረጋገጡ ተጨማሪ ማብራሪያ ከመድረኩ ተስጥቷል፡፡
በመጨረሻም ከሪፖርት አቅራቢ አካላት በሚቀርቡ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀት፣ አቀራረብ ደረጃዎች ወጥነት፣ ትክክለኛነትና ተዛማጅነት ላይ የጋራ ግንዛቤ መፍጠር እጅግ አስፈላጊ መሆኑ ሁሉም አካላት ግመንዛቤ በመያዝ ለቅንጅታዊ ሥራዎች ተቀራርበን መስራት እንደዋነኛ ተግባር እንዲሆን በማድረግ የተሻለ አሠራር የማምጣት ኃላፊነት እዚህ የተገኘው ጭምር የተቆጣጣሪ አካላት መሆኑን ልንገነዘበው ይገባል በሚሉ ጭብጦች የጋራ አቅጣጫ በመያዝ ተጠናቋል፡፡