ቦርዱ አሠራሮቹን በቅጥርና በምደባ ላገኛቸው ሠራተኞች አስተዋወቀ

==================================

 ሰኔ 8 ቀን 2015 ዓ.ም.

አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ በቅጥርና በምደባ ከፌዴራል ሲቪል ኮሚሽን ለመጡ ሠራተኞች የተቋሙን አሠራሮችን ለማስገንዘብ በቦርዱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የትውውቅ ፕሮግራም ተካሄደ፡፡

በትውውቁ ፕሮግራም ላይ የተገኙት አቶ ፍቃዱ አጎናፍር የቦርዱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር በቅጥርና በምደባ ወደ ተቋሙ የተቀላቀሉትን ሠራተኞች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ቦርዱ በዋናነት አራት ዓላማዎች ያሉት መሆኑን ጠቁመው በየተመደባችሁበት ቦታ ብቻ ሳይሆን የሥራ ልምድ በማጥናት ለቦርዱ በተሻለ አገልግሎት እና ጥቅም እንድትሰጡ የሚያስችላችን ቦታ ለመመደብ እንደገና ምደባ የምናካሂድ መሆኑን ለማስገንዘብ እፈልጋለሁ ካሉ በኋላ ሠራተኞች እርስ በእርስ እንዲተዋወቁ አድርገዋል፡፡

በመቀጠል አቶ ደረሰ መለስ የብቃትና ሰው ሀብት አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ ሠራተኞች በየተመደቡበት የሥራ ቦታዎች የሚሰጣቸውን ሥራዎች በአግባቡ እንዲወጡ የሚያስችላቸው ቅድመ መረጃ እንዲኖራቸው የቦርዱ መዋቅራዊ አደረጃጀትና አሠራሮች ዙሪያ ገለፃ በማድረግና ተጨማሪ መረጃዎችን በመስጠት ተቋሙን አስተዋውቀዋል፡፡