የኢትዮዽያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ለሁሉም ዕውቅና የሰጣቸው የሂሳብ እና ኦዲት ሙያተኞች በየዓመቱ የግልና የድርጅት የሙያ ፈቃድ ዕድሳት የሚያከናውን መሆኑ ይታወቃል፡፡
በዚሁም መሰረት  የ2012 ዓ.ም የግል የሙያ ፈቃድ ዕድሳት ከሀምሌ 1- ሀምሌ 30/ 2011 ዓ.ም የተከናወነ ሲሆን  የ2012 ዓ.ም የድርጅት የሙያ ፈቃድ ዕድሳት ከነሀሴ 1/2011 ዓ.ም -ታህሳስ 30/2012 ዓ.ም  መሆኑን አውቃችሁ እድሳቱን በጊዜ ሰሌዳ መሰረት በኢ-ሰርቪስ እንድታከናውኑ እናሳውቃለን፡፡
የኢትዮዽያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ