ቀን 21/03/2015 ዓ.ም.

ማስታወቂያ

ለሂሳብና ኦዲት ባለሙያዎችና ድርጅቶች በሙሉ

ባሉበት

ጉዳዩ፡- የድርጅት ምዝገባ የሙያ ፍቃድ እድሳትን የመለከታል፣

በኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ የሂሳብ እና ኦዲት ሙያ ድርጅቶች ምዝገባ በማከናወን የሂሳብ እና የኦዲት ሙያ አገልገሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ ድርጅቶች በቦርዱ መመሪያ ቁጥር 805/2013 አንቀጽ 7 መሠረት በየዓመቱ ማሳደስ እንዳለባቸዉ ተደንግጓል። በዚሁ መሠረት ቦርዱ ከታህሳስ 1/2015 ጀምሮ ነባር የምዝገባ ምስክር ወረቀት ለ2015/2016 እድሳት ለመጀመር ዝግጅት ላይ ይገኛል።

ስለዚህ ማንኛዉም የሂሳብ ወይም የኦዲት ድርጅቶች የታደሰ የምዝገባ ምስክር ወረቀቱን ለማግኘት ከታህሳስ 1/2015 እስከ ጥር 30/2015 ድረስ በቦርዱ ኢሠርቪስ ለእድሳቱ የሚያሰፈልጉትን መስፈርቶች በሙሉ አሟልታችሁ እንድትመዘገቡ ከወዲዉ በትህትና እንገልጻለን።

ማስገንዘቢያ፡

  • ከጥር 30/2015 በኃላ በኢሰርቪስ ላይ የሚሞላ የእድሳት ማመልከቻ በመመሪያዉ መሠረት በቅጣት የሚትሰተናገዱ መሆኑን ለማስገንዘብ እንወዳለን።
  • ማንኛዉም የሂሳብ ወይም የኦዲት ድርጅቶች ለእድሳቱ የሚያሰፈልጉትን መስፈርቶች በሙሉ አሟልተዉ ካላመለከቱ በቅጣት የሚስተናገዱ ይሆናል።
  • ማንኛዉም የሂሳብ ወይም የኦዲት ድርጅቶች ለእድሳቱ በኢሠርቪስ መስፈርቶችን በሙሉ በትክክል አሟልተዉ ካመለከቱ በኋላ በአጭር የጹሑፍ መልዕት (SMS) እንድትመጡ ካልተነገራችሁ በስተቀር ወደ ቦርዱ በአካል መቅረብ አይጠበቅባችሁም።
  • የቦርዱን ሠራተኞች የፍቃድ እድሳት ማመልከቻ በኢሰርቪስ ማስሞላት አይቻልም።
  • ለኢሠርቪስ አሞላል በአካል መቅረብ ሳይጠበቅባችሁ በስልክ ቁጥር 0118121949/0118120989 ላይ በመደወል የምክር አገልግሎት በመጠየቅ ባለሙያዉ ባለበት ቦታ ሆኖ ኢሠርቪስን መሙላት ይችላል።

የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ