10/05/2015 ዓ.ም
ለሒሳብ እና ለኦዲት ሙያ ድርጅት ባለቤቶች በሙሉ
ጉዳዩ፡ የአገልግሎት ክፍያን ይመለከታል
የኢትዮጵያ የሒሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ለጥምቀት በዓል በሠላም አደረሳችሁ እያለ በደንብ ቁጥር 481/2013 መሠረት ቦርዱ ለሚሰጣቸዉ አገልግሎቶች ክፍያን እንደሚያስከፍል ይደነግጋል።
በዚህም መሠረት የሒሳብ ወይም የኦዲት ሙያ ድርጅት ባለቤቶች የ2015/16 በጀት ዓመት የሙያ ፈቃድ ምስክር ወረቀት ዕድሳት የአገልግሎት ክፍያችሁን በመመሪያዉ መሠረት በቴሌብር በመክፈል እንድታሳድሱ እየጠየቅን፤
ከዚህ በፊት የግል የሒሳብ/የኦዲት (Individual Certificate) ሙያ ፈቃድ የምስክር ወረቀት ለ2014 ለማሳደስ የአገልግሎት ክፍያ የከፈላችሁና አገልግሎቱን ያገኛችሁ በሙሉ የ2015/16 በጀት ዓመት የሙያ ምዝገባ ፈቃድ ምስክር ወረቀት ዕድሳት የአገልግሎት ክፍያዉ የሚመለከታችሁ ስለሆነ የምትከፍሉ መሆኑን እያሳወቅን ሆኖም ግን ለ2014 ለግል የሒሳብ/የኦዲት የምስክር ወረቀት (Individual Certificate) ከፍላችሁ አገልግሎቱን ያላገኛችሁ ማለትም ሁለት ጊዜ ክፍያ ፈጽማችሁ የግሉን ያላሳደሳችሁ መረጀዉን አያይዛችሁ ስታቀረቡ የምናሰተናግድ መሆኑን እንገልጻልን።
ማሳሰብያ፡- የሒሳብ ወይም የኦዲት ሙያ የምዝገባ ምስክር ወረቀት እድሳት እስከ ጥር 30/2015 ብቻ የሚቆይ መሆኑን አዉቃችሁ አላስፈላጊ ቅጣት ዉስጥ ከመግባት ከወዲሁ አስፈላጊዉን መሥፈርት በማሟላት ፎርሙን በኢሰርቪሱ ብቻ ሞልታቸዉ እንዲታሳድሱ እናሳስባለን።
የኢትዮጵያ የሒሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ
Leave A Comment
You must be logged in to post a comment.