ለሪፖርት አቅራቢ አካላት በሙሉ

የኢትዮዽያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ ለተጠቃሚዎች ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች ዋነኞቹ

  1. ሪፖርት አቅራቢ አካላትን የህዝብ ጥቅም ያለባቸው ወይም አነስተኛ እና መካከለኛ ድርጅቶች ብሎ መለየት የሚያስችል መስፈርት የማውጣት እና የመመዝገብ እንዲሁም
  2. የሪፖርት አቅራቢ አካላትን የሂሳብ መግለጫዎች ተቀብሎ የመመዝገብ ተግባራት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

ቦርዱ ለነዚህ እና መሰል ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች በመንግስት በሚወሰነው ተመን መሰረት ክፍያ እንደሚያስከፍል በአዋጅ 847/2006 በተሰጠው ኃላፊነት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 481/2013 ዓ.ም የአገልግሎት የክፍያ ደንቡ ጸድቆ ተግባራዊ ሆኗል፡፡

ይህን መሰረት በማድረግ ቦርዱ ባወጣው የሪፓርት አቅራቢ አካላት መለያ መስፈርት የሂሳብ መግለጫዎቻችሁን በዓለም ዓቀፍ የፋይናንስ ሪፓርት አዘገጃጀት እና አቅራረብ ደረጃዎች መሰረት መተግበር ያለባችሁ የሪፓርት አቅራቢ አካላት ከትግበራ በፊት ለድርጅታችሁ የሚገባውን ደረጃ (IFRS, IFRS for SMES ወይም IPSAS) በመለየት፣ የሂሳብ መግለጫዎቻችሁን በነዚሁ ደረጃዎች መሰረት በማዘጋጀት እና ኦዲት በማስደረግ ወደ ቦርዱ ማቅረብ እንዳለባችሁ ይታወቃል፡፡

በዚሁ መሰረት

  1. የህዝብ ጥቅም ያለባችሁ ወይም ምዝገባችሁ (PIE, ECX, COOP እና CHA) የሆነ ሪፓርት አቅራቢ አካላት የሂሳብ መግለጫዎቻችሁን በቦርዱ ስታስመዘግቡ የአገልግሎት ክፍያ ብር 685.00 (ስድስት መቶ ሰማንያ አምስት ብር) እና
  2. የአነስተኛ ወይም መካከለኛ ድርጅቶች ብር 540.00(አምስት መቶ አርባ ብር) በኢትዮዽያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000393097667 ክፍያ በመፈጸም እና የባንክ ዲፖዚቱን ይዛችሁ በመቅረብ አገልግሎቱን ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡- ቀድሞ ደረጃዎቹን የተገበራችሁ እና በትግበራ ሂደት ያላችሁ ሪፖርት አቅራቢ አካላት በጀመራችሁት እንድትጨርሱ እንመክራለን፡፡

ከሰላምታ ጋር

የኢትዮዽያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ