የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ በአዎጅ ቁጥር 847/2006 አንቀፅ 4 (2) (መ) የሪፖርት አቅራቢ አካላትን የህዝብ ጥቅም ያለባቸው ወይም አነስተኛና መካከለኛ በሚል መለየት የሚያስችል መስፈርቶችን በማውጣት እንዲመዘግብ ስልጣን የተሰጠው መሆኑ ይታወቃል፡፡
እንዲሁም ደግሞ በአንቀፅ 8 (1) እና 4(2) (ሸ) ማንኛውም ሪፖርት  አቅራቢ አካል ቦርዱ በሚያወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የሂሳብ መግለጫውን ለቦርዱ  ማቅረብ እንዳለበት፤  ቦርዱ አነዚህን ሪፖርቶች የመገምገምና ፍላጎት ላላቸው ባለድርሻ አካላት ተደራሽ የሚሆኑበትን ሁኔታ እንዲያመቻች ተደንግጓል፡፡
በዚሁ መሠረት ቦርዱ የሪፖርት አቅራቢ አካላት ከነባሩ አሰራር ወደ አለምአቀፍ ደረጃዎች የሚደርጉነትን ሽግግር በተሳካ ሁኔታ ለማስተግበር የትግበራ ፍኖተ-ካርታ አዘጋጅቶ ሪፖርት አቅራቢ ድርጅቶችን ለመመዝገብ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡
በመሆኑም በኢ.ፌ.ድ.ሪ የገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን  የከፈተኛ ግብር ከፋዮች የሆናችሁ በሙሉ ከዚህ ቀጥሎ በወጣላችሁ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ በአካል በመገኘት ድርጅታችሁን እንድታስመዘግቡ  እናስታውቃለን፡፡
የምዝገባ የጊዜ ሰሌዳ 
ተመዝጋቢዎች– -ከፍተኛ ግብር ከፋዮች
የምዝገባ ቀናት – ከሰኔ 22/2009  እስከ  ሀምሌ 28/20 09ዓ.ም ባሉት የስራ ቀናት
የምዝገባ ቦታ  -የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ፣ስድስት ኪሎ ማዳጋስካር መንገድ  ሊደርሺፕ ህንጻ 4ኛ ፎቅ
ለበለጠ መረጃ፡ የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ድረ-ገጽ፡ www.aabe.gov.et
በስልክ ቁጥር +251 111 54 09 10፤+251-11 1 54 09 00፤+251 11 1 54 09 13 በመደወል ወይም ስድስት ኪሎ ማዳጋስካር መንገድ  ሊደርሺፕ ህንጻ 4ኛ ፎቅ ከሚገኘው የቦርዱ ቢሮ በአካል በመቅረብ ዝርዝር መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡