የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ በአዎጅ ቁጥር 847/2006 አንቀፅ 4 (2)(መ) የሪፖርት አቅራቢ አካላትን የህዝብ ጥቅም ያለባቸው ወይም አነስተኛና መካከለኛ በሚል መለየት የሚያስችል መስፈርቶችን በማውጣት  እነዲመዘግብ ስልጣን የተሰጠው መሆኑ ይታወቃል፡፡

እንዲሁም ደግሞ በአንቀፅ 8 (1) እና 4(2)(ሸ) ማንኛውም ሪፖርት  አቅራቢ አካል ቦርዱ በሚያወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የሂሳብ መግለጫውን ለቦርዱ  ማቅረብ እንዳለበት፤  ቦርዱ አነዚህን ሪፖርቶች የመገምገምና ፍላጎት ላላቸው ባለድርሻ አካላት ተደራሽ የሚሆኑበትን ሁኔታ እንዲያመቻች ተደንግጓል፡፡

በዚሁ መሠረት ቦርዱ የሪፖርት አቅራቢ አካላት ከነባሩ አሰራር ወደ አለምአቀፍ ደረጃዎች የሚደርጉነትን ሽግግር በተሳካ ሁኔታ ለማስተግበር የትግበራ ፍኖተ-ካርታ አዘጋጅቶ ሪፖርት አቅራቢ ድርጅቶችን ለመመዝገብ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

በመሆኑም በኢ.ፌ.ድ.ሪ የገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን የታክስ አከፋፈል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤታችሁ መሰረት በአዲስ አበባ የምትገኙ ግብር ከፋዮች የሆናችሁ እና የ2008 ዓ.ም አጠቃላይ አመታዊ ሽያጫችሁ ከአንድ ሚሊዮን(1,000,000)ብር በላይ የሆነ ወይም ድርጅት/ኩባንያዎች(Share companies and privet limited companies)የሆናችሁ በሙሉ፡፡ከዚህ ቀጥሎ  በወጣላችሁ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ በአካል በመገኘት ድርጅታችሁን እንድታስመዘግቡ  እናስታውቃለን፡፡

  የምዝገባ የጊዜ ሰሌዳ ፡ሀ

ተ.ቁ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የምዝገባ ቀናት የምዝገባ ቦታ
1 ልደታ  

ከሰኔ 15/2009 እስከ  ሀምሌ 28/20 09ዓ.ም ባሉት የስራ ቀናት

 

የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ፣ስድስት ኪሎ ማዳጋስካር መንገድ  ሊደርሺፕ ህንጻ 4ኛ ፎቅ

 

2 አቃቂ ቃሊቲ
3  አዲስ ከተማ
4 አራዳ
 

 

5 መርካቶ ቁጥር አንድ ከነሐሴ1/2009 ዓ.ም እስከ መስከረም 30/2010ዓ.ም ባሉት የስራ ቀናት የስራ ቀናት

 

የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ፣ስድስት ኪሎ ማዳጋስካር መንገድ  ሊደርሺፕ ህንጻ 4ኛ ፎቅ

 

6 መርካቶ ቁጥር ሁለት
7 ጉለሌ
8 ቂርቆስ
 

 

9 አዲስ አበባ  ቁጥር 1 ከጥቅምት01 /2010ዓ.ም አስከ ህዳር 29 /2010ዓ.ም ባሉት የስራ ቀናት የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ፣ስድስት ኪሎ ማዳጋስካር መንገድ  ሊደርሺፕ ህንጻ 4ኛ ፎቅ

 

10 አዲስ አበባ ቁጥር 2
11 የካ
12 ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ
 

 

13 ቦሌ ከታህሳስ 02/2010ዓ.ም እስከ  ታህሳስ 30/2010ዓ.ም ባሉት የስራ ቀናት የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ፣ስድስት ኪሎ ማዳጋስካር መንገድ  ሊደርሺፕ ህንጻ 4ኛ ፎቅ
14 ኮ/ቀ/ክ/ከተማ
15 ምዕራብ አዲስ አበባ
16 ምስራቅ አዲስ አበባ

 

 

የምዝገባ የጊዜ ሰሌዳ ፡ ለ

ተመዝጋቢዎች የምዝገባ ቀናት የምዝገባ ቦታ
ከፍተኛ ግብር ከፋዮች በሙሉ ከሰኔ 22/2009  እስከ  ሀምሌ 28/20 09ዓ.ም ባሉት የስራ ቀናት የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ፣ስድስት ኪሎ ማዳጋስካር መንገድ  ሊደርሺፕ ህንጻ 4ኛ ፎቅ
 

 

 

የፌደራል  የመንግስት የልማት ድርጅቶች በአጠቃላይ

ከነሐሴ 1/2009 ዓ. ም እስከ ጥቅምት 30/2010ዓ.ም ባሉት የስራ ቀናት የስራ ቀናት የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ፣ስድስት ኪሎ ማዳጋስካር መንገድ  ሊደርሺፕ ህንጻ 4ኛ ፎቅ
የአዲስ አበባ ከተማ   አስተዳደር የመንግስት የልማት ድርጅቶች በሙሉ
የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት

የመንግስት የልማት ድረጅቶች በሙሉ

የኢትየጵያ ምርት ገበያ ባለስልጣን  የግብይት አባላት (ECX Members)በሙሉ
በብሄራዊ ባንክ ቁጥጥር የሚደረግባቸው የፋይናንስ ተቋማት  (ባንኮች፡፡ኢንሹራንሶች፡የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት፡የሊዝ ፈይናንሲንግ ተቋማትእና የመሳሰሉት)
የህብረት ስራ ማህበራት ባጠቃላይ

 

 

ለበለጠ መረጃ፡

የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ድረ-ገጽ፡ www.aabe.gov.et   እንዲሁም ፌስኩክ ገጽ፡ facebook.com/AABE.Ethiopia ይጎብኙ

ከቦርድ ድረ-ገጽ ላይ የመመዝገቢያ ቅጾች ፣ መሟላት ስላለባቸው ዝርዝር ማስረጃዎች እና ሎሎች ጠቃሚ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡

ወይም በስልክ ቁጥር +251 111 54 09 10፤+251-11 1 54 09 00፤+251 11 1 54 09 13 ይደውሉ

ቦርዱ አድራሻ፡  ስድስት ኪሎ ማዳጋስካር መንገድ  ሊደርሺፕ ህንጻ 4ኛ ፎቅ