ዓለም ዓቀፍ የፋይናንስ ሪፓርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ደረጃዎች (IFRS, IFRS for SMEs and IPSAS) ትግበራ የኢትዮጽያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ባስቀመጠው የትግበራ ፍኖተ-ካርታ መሰረት እየተከናወነ ይገኛል፡፡
ሁሉንም መስፈርቶች የሚያሟሉ አካላትም በወቅቱ በቦርዱ በአካል በመገኘት ወይም በመንግስት የኤሌክትሮኒክ አገልግሎት (e-service) በመጠቀም ድርጀታቸውን አስመዝግበው ለድርጀታቸው የሚገባውን ደረጃ እየተገበሩ ይገኛሉ፡፡
ከፍተኛ የህዝብ ጥቅም ያለባቸው ሪፖርት አቅራቢ አካላት ከ2010 ዓመት ጀምሮ ዓመታዊ የፋይናንስ ሪፓርታቸውን በFUII IFRS እና ሌሎችም ሪፖርት አቅራቢ አካላት በዚያው ልክ ወደ ቦርዱ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡
ቦርዱም አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር የሚያደርግ ሲሆን በአዋጅ 847/2006 መሰረት የሽግግር ወቅቱ ከ2012 ዓ.ም የማያልፍ /የማይራዘም መሆኑ ታውቆ ወደ ዝግጀት ያልገባችሁ አካላት ከወዲሁ ወደ ትግበራ እንድትገቡ እንገልጻለን
የኢትዮጽያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ
Leave A Comment
You must be logged in to post a comment.