የኢትዮጲያ የሂሳብ አያየዝ እና ኦዲት ቦርድ
የኢትዮጲያ የሂሳብ አያየዝ እና ኦዲት ቦርድ በአዋጅ ቁጥር847/2006 መሰረት በደንብ ቁጥር 332/2007 የተቋቋመ ተቆጣጣሪ መንግስታዊ ድርጅት ነው.
የኢትዮጲያ የሂሳብ አያየዝ እና ኦዲት ቦርድ
ዓለም አቀፋዊ እውቅና ያለን በኢትዮጵያ ውስጥ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ሙያን በተሳካ ሁኔታ የሚቆጣጠር ገለልተኛ ተቆጣጣሪ አካል ሆኖ መገኘት ነው፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያለው የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀት እና አቀራረብን በማረጋገጥ ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋና የህዝብ ጥቅም እንዲጠበቅ ድጋፍ ማድረግ ሲሆን፣ ይህንንም ለማስቻል በሂሳብ አያያዝና ኦዲት ሙያ ላይ ህጎች፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች እና የዓለም አቀፍ ደረጃዎች በሚጠይቁት መሰረት ተገቢ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ ነው፡፡
በማያቋርጥ የለውጥ ዑደት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየረቀቁና እየተወሳሰቡ የሚሄዱ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ፍላጎቶች የሚንፀባረቁበትን የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ሙያን በኢትዮጵያ ውስጥ እንድንቆጣጠር በሕግ የተሰጠንን ኃላፊነት ለመወጣት በምናከናውናቸው ተግባራት በሙሉ የምናከብራቸውና የምንመራባቸው እሴቶቻችን የሚከተሉት ናቸው፡፡