aabe-strategic-plan-amharic

aabe-strategic-plan-english

 

 

ራዕይ

ዓለም አቀፋዊ እውቅና ያለን በኢትዮጵያ ውስጥ የሂሳብ አያያዝና  ኦዲት  ሙያን  በተሳካ  ሁኔታ  የሚቆጣጠር ገለልተኛ  ተቆጣጣሪ  አካል  ሆኖ  መገኘት  ነው፡፡

ተልዕኮ

በኢትዮጵያ  ውስጥ  ከፍተኛ  ጥራት  ያለው የፋይናንስ ሪፖርት   አዘገጃጀት   እና   አቀራረብን   በማረጋገጥ ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋና የህዝብ ጥቅም እንዲጠበቅ ድጋፍ ማድረግ በሂሳብ አያያዝና ኦዲት ሙያ ላይ ህጎች፣ ደንቦች፣  መመሪያዎች  እና  የዓለም  አቀፍ  ደረጃዎች በሚጠይቁት መሰረት ተገቢ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ ነው፡፡

 

እሴቶች

በማያቋርጥ የለውጥ ዑደት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየረቀቁና እየተወሳሰቡ የሚሄዱ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ፍላጎቶች የሚንፀባረቁበትን የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ሙያን በኢትዮጵያ ውስጥ እንድንቆጣጠር በሕግ የተሰጠንን ኃላፊነት ለመወጣት በምናከናውናቸው ተግባራት በሙሉ የምናከብራቸውና የምንመራባቸው እሴቶቻችን የሚከተሉት ናቸው፡፡

 

  • ታማኝነት
  • ሚዛናዊነት
  • ተባባሪነት
  • ተጠያቂነት
  • ችግር ፈቺነት
  • ለልህቀት ያለ ቁርጠኝነት

 

የምንመራባቸው ፖሊሲዎች

  • በክትትልና ቁጥጥር ፣  ሕግን   በማስከበር  እና በትምህርትና ስልጠና ዙሪያ የምንሠራቸውን ሥራዎች ውጤታማነት ከፍ ለማድረግ በተቻለ መጠን በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ከሚገኙ አግባብ ካላቸው አካላት ጋር መተባበር እና ግብዓቶችን በጋራ መጠቀም፤
  • ኃላፊነታችንን በመወጣት ረገድ እንቅፋት (ችግር) ሊፈጥሩ  የሚችሉ  አዳዲስ የሚከሰቱ ሥጋቶችን፣ የንግድና የገበያ እንቅስቃሴ አጠቃላይ አቅጣጫዎችን ወዘተ…  በተሻለ  ሁኔታ   ለመገመትና  የትኩረት አቅጣጫዎችን ለመለየት የሚያስችል በስጋት ላይ የተመሰረተ   የአሰራር   ሥርዓቶችን  መከተል፤
  • የአገልግሎት አሰጣጣችንን ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ተደራሽ ለማድረግ  እና  ተገልጋዩ  ሕዝብ መረጃ በቀላሉ  የሚያገኝበትን  ሁኔታ  ለመፍጠር አቅም በፈቀደ  መጠን  ዘመናዊ  የመረጃና  የመገናኛ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም፤
  • ዘለቄታዊነት ያለው ተቋማዊ ልህቀትን ለመፍጠር መስራት፤

ቁልፍ ስራ መስኮች

  1. የሙያ ደረጃዎችን ደንቦችንና መመሪያዎችን ማውጣት

ላማ

ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ያላቸውና ዓለም አቀፍ ተቀባይነትን ያገኙ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ደረጃዎች፣ የኦዲት ደረጃዎች፣  የሙያ ሥነ-ምግባር መመሪያዎች እና የድርጅት መልካም አስተዳደር መመሪያዎችን በመቀበልና በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲተገበር በማድረግ ኢንቨስተሮችና ሌሎች   የፋይናንስ   ሪፖርት   ተጠቃሚዎች   በሂሳብ መግለጫዎች ላይ የሚኖራቸውን አመኔታ ማረጋገጥ፡

ግብ

ለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ፣ የፐሊክ  ሴክተር  የሂሳብ አያያዝ፣  የኦዲት ሙያ ስነምግባር እና የድርጅት መልካም አስተዳደር ደረጃዎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች እንዲሁም ለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያላቸው መልካም ተሞክሮዎችን መሰረት በማድረግ በሀገር ውስጥ ተፈጻሚ የሚሆኑ ደረጃዎችንደንቦችንና መመሪያዎችን ማውጣት፡፡

ግብ

ሀገራችንን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘቡ እና ዘርፍ ነክ የሆኑ ጉዳዮችን ከግምት ውስጥ ያስገቡ ቴክኒካል መመሪያዎች፣ ቴክኒካል ማብራሪያዎች፣ የተግባር ማጣቀሻ ማንዋሎች እና ሌሎች አጋዥ ሰነዶችን ዘጋጅቶ ማውጣት ዓለም አቀፍ ደረጃዎቹ በተሳካ ሁኔታ እንዲተገበሩ የተመቸ ሁኔታ መፍጠር፡፡

ግብ

የዓለም አቀፍ የደረጃዎች አውጭ ቦርዶች በሚካሄደው የደረጃዎች ማውጣት ሂደት ላይ በንቃት በመሳተፍ ለም አቀፍ የደረጃዎች አወጣጥ ላይ ተፅዕኖ ለማሳረፍ ጥረት ማድረግ፡፡

  1. የኦዲት ጥራት ክትትል እና ግምገማ

ላማ

ውጤታማ በሆነ የኦዲት አሰራር ግምገማና ክትትል ኢንቨስተሮች እና ሌሎች የሂሳብ መግለጫ ተጠቃሚዎች ኦዲት በሆኑ የሂሳብ መግለጫዎች ላይ እምነት እንዲኖራቸው ማድረግ፡፡

ግብ

አቅምና ብቃት ያለው የኦዲት ግምገማ እና ክትትል መምሪያ ማቋቋምና የሚከተለውም የአሰራር ስርዓት ኦዲት ውድቀት ሊፈጥሩ የሚችሉ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ጋር የተገናኙ ዲስ ጉዳዮችን ሌሎች ቁልፍ የስጋት ክፍሎችን ለመለየትና ለመገምገም የሚያስችሉ የስጋት ግምገማ ዘዴዎችን በመጠቀም ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ማድረግ፡፡

ግብ

ከፍተኛ ጥራት ያለው ኦዲት ለማከናወን እና በኦዲት ተቋም አሰራር ውስጥ የጥራት ቁጥጥርን በስራ ላይ በማዋል ረገድ የዓለም አቀ የኦዲት እና የማረጋገጥ ስራዎች አገልግሎት ደረጃዎች ቦርድ (IAASB) አነስተኛና መካከለኛ የኦዲት ተቋማት ያዘጋጃቸውን መመሪያዎችን አና የአሰራር ማዕቀፎችን ማሰራጨት እና ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን መስራት፡፡

ግብ

የኦዲት ድርጅቶች፣ ፐብሊክ ኦዲተሮች እና የተመሰከረቸው ኦዲተሮችኦዲት ስራዎችን የኦዲት ደረጃዎችን፣ መመሪያዎችን፣ ደንቦችን እና በስራ ላይ ያሉ ህጎችን፣ ሳይከተሉ (ሳያከብሩ) ያከናውኑ የሚችሉባቸውን ሁኔታችን በመለየት መሰረታዊ ምክንያቶችን ለማወቅ ምርመራ ማድረግ እንዳስፈላጊነቱ ተገቢውን እርምጃ መውሰድ፡፡

ግብ

በኢትዮጵያ ውስጥ የዓለም አቀፍ ደረጃዎች በአግባቡ መተግበራቸውን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ቁጥጥር ለማጠናከር ከሌሎች የዘርፍ ተቆጣጣሪዎች ጋር የተሳካ የቅንጅትና የትብብር ሥራ መስራት፡፡

ግብ

አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተሳትፎአችንን ለማስጠበቅ ከአህጉራዊ የኦዲት ተቆጣጣሪ አካላት እና ከዓለም አቀፉ ገለልተኛ የኦዲት ተቆጣጣሪ ፎረም ጋር በትብብር መስራት፡፡

  1. ፋይናንስ ሪፖርቶች አዘገጃጀትና አቀራረብ ግምገማ እና ክትትል

ላማ

ውጤታማ በሆነ የሂሳብ መግለጫዎች ግምገማ እና ክትትል ኢንቨስተሮችን   ጨምሮ   ሌሎች   የሂሳብ   መግለጫ ተጠቃሚዎች   በሪፖረት   አቅራቢዎች   ተዘጋጅተው በሚቀርቡ የሂሳብ መግለጫዎች ላይ እምነት እንዲኖራቸው ማድረግ፡፡

ግብ

አቅምና ብቃት ያለው ፋይናንስ ሪፖርቶች አዘገጃጀትና አቀራረብ ግምገማ እና ክትትል መምሪያ ማቋቋምና የሚከተለውም የአሰራር ስርዓት የዓለም አቀፍ ፋይናንስ ሪፖርቶች አዘገጃጀትና አቀራረብ ደረጃዎችን እና አስገዳጅ የህግ ፍላጎቶችን ያልተከተሉ የሂሳብ መግለጫዎችን ሊፈጥሩ የሚችሉ ሂሳብ አያያዝ ፋይናንስ ሪፖርቶች አዘገጃጀትና አቀራረብ ጋር የተገናኙ ዲስ ጉዳዮችን ሌሎች ቁልፍ የስጋት ክፍሎችን ለመለየትና ለመገምገም የሚያስችሉ የስጋት ግምገማ ዘዴዎችን በመጠቀም ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ማድረግ፡፡

ግብ

የሂሳብ መግለጫዎችን ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ደረጃዎች መሰረት ለማዘጋጀት የወጡ  የትግበራና ቴክኒካል መመሪያዎች የማስተዋወቅና የግንዛቤ ስጨበጥ ሥራ መስራት እና ሰነዶችን ማሰራጨት፡፡

ግብ

አሳሳች የሂሳብ መግለጫዎችን ለማዘጋጀት ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ ከሂሳብ አያያዝ ጋር የሚገናኙ ዲስ የሚከሰቱ ጉዳዮችና ሌሎች ቁልፍ የሆኑ ፋይናንስ ሪፖርቶች አዘገጃጀትና አቀራረብ ስጋቶችን መለየት፡፡

 

  1. የሙያ ትምህርት፣ ስልጠና፣  የሙያ ማጎልበቻ  የብቃት  ማረጋገጥ   እውቅና  መስጠት

ላማ

በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ጥራት ያለው የሂሳብ አያያዝና የኦዲት ሙያ ትምህርት እንዲጎለብትና እንዲስፋፋ በማድረግ ከፍተኛ ጥራት ያለው የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ትግበራን ማረጋገጥ፡፡

ግብ

በማደግ ላይ የለውን ኢኮኖሚ ተከትሎ የሚጨምረውን የሂሳብ አያያዝና የኦዲት ሙያ አገልግሎት የገበያ ፍላጎት ለሟሟላት የሚያስችል በቂ ብዛትና ብቃት ያላቸው የሂሳብ ባለሙያዎች እና ኦዲተሮች እንዲኖሩ ማድረግ፡፡

ግብ

የዓለም አቀፉን የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀት አቀራረብ ደረጃዎች በሀገራችን በተሳካ ሁኔታ ተግባ ለማድረግ በሪፖርት አቅራቢ ድርጅቶች ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ የሂሳብ ባለሙያዎች ደረጃዎቹን ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችል ሙያዊ ብቃት እንዲኖራቸው ማድረግ፡፡

 

  1. ምርመራና ህግ ማስከበር

ላማ

በኢትዮጵያ ውስጥ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ሙያን ተአማኒነት መገንባት፡፡

 

ግብ

የሂሳብ አያያዝና የኦዲት ሙያን ለመቆጣጠር በተሰጠን ኃለፊነት ላይ ተመስርተን ጠንካራ ምርመራና ህግ ማስከበር ስርዓትን ማስፈን፡፡