በህተም/ቤት የገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
የተከበሩ ወ/ሮ ለምለም ሓድጎ ያደረጉት ንግግር
-የተከበሩ ወ/ሮ ሂክመት አብደላ ፣የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ዋና ዳይሬክተር፣
-የተከበራችሁ የሀገራችን የሚዲያ ተቋማት ተወካዮችና የዚህ መድረክ ተሳታፊዎች፣
ክብራትና ክብራን፡
በመጀመሪያ በዚህ በሀገራችን የዴሞክራሲ ተቋም አንድ አካል እና የዕድገታችን ማጠንጠኛ በሆኑ የሚዲያ ባለሙያዎች ፊት ቀርቤ ንግግር እንዳደርግ ዕድሉ ስለተሰጠኝ የተሰማኝን ታላቅ ደስታ ለመግለጽ እወዳለሁ።
ባደጉና በበለጸጉ ሀገራት ሚዲያ እንደ አራተኛ መንግስት ይቆጠራል ሲባል የሀገሪቱ የኢኩኖሚ፣ የማህበራዊ እና ፓለቲካዊ ስርዓት ግንባታ ለህዝብ ተጠቃሚነት ያለውን ቀጥተኛ ሚና የሚያሳድግ እና ይህ ሳይሆን ቢቀር የመንግስትን እጅ እስከመጠምዘዝ የሚችል ኃይል መሆኑን በማመንና በመረጋገጡም ችምር ነው፡፡ ከዚህ አንጻር በእውነተኛ የሙያ ፍቅር እና ስነ ምግባር የታነጹ ሙያተኞች የተደራጁ የሚዲያ ተቀማት በመንግስት እና በዜጎቻቸው መካከል ጠንካራ ድልድይ በመሆን ወገንተኝነታቸውን ለሀገርና ለሀገር ብቻ ያደርጉ ሳይናወጡ ኃያልነታቸውን እንዳስከበሩ ዘመናትን ይሻገራሉ ተሻግረዋልም።
ክቡራትና ክቡራን
ሀገራችን የበርካታ ዘመናት ዘርፈ ብዙ ታሪኮች ባለቤት፣ ብዙ ሊባልላት የሚገባና በዘመናት የመንግስታት ቅብብሎሽ አለመጣጣም በተገቢው ያልተሰራበት ዘርፍ ቢኖር ቀዳሚው ሚዲያው መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡
ከዚያም አልፎ “ስራው እራሱ ይናገራል” በሚል ብሂል የሰሩትን አለመናገር ደግሞ እስከነችግሩም ቢሆን ሚዲያውን ረሃብተኛና ውሱን እንዲሆን እድል ፈጥሯል፡፡ ያለንን ውሱን ሀብት በተገቢው ዓላማ ላይ አውለንና ህዝብን ተጠቃሚ በማድረግ የተጫነብንን ድህነት ለመቅረፍ በምናደረገው እንቅስቃሴ የውሸት ሪፓርቶች መበራከት፣ ለግል ጥቅም ቅድሚያ መስጠት የሚዲያ ተቋማት በተለያዩ አካላት ጫና ስር መውደቅና ወገንተኝነትን ማዛባት ለሚዲያውም ሆነ ለሀገር የቁልቁለት ጉዞ ሚናው ከፍተኛ ነው፡፡
ይህ በንዲህ እያለ ያሉንን የሚዲያ አውታሮች በሚገባ አበልጽገን ለዕድገት ማዋል ሳንችል ቴክኖሎጂው የያንዳንዱ ዜጋ መዳፍ ውስጥ መግባት መቆጣጠርና ማስተናገድ ወደማንችለው ደረጃ ደርሶ ለርስበርስ መጠፋፊያ ለመሆን መብቃቱ የቅርብ ጊዜ የሰሜን አፍሪካ ሀገራትና የሀገራችንም ትዝታ ነው።
የተከበራችሁ የመድረኩ ተሳታፊዎች
ሚዲያን በዋነኝነት ሚዲያ ከሚያሰኛቸው ነገሮች አንዱ መረጃ መሆኑን ለዚህ መድረክ መናገር ባያስፈልግም ግን ደግሞ የሚቀርበው መረጃ ትክክለኛ እና አመኔታ የሚጣልበት፣ በተገቢው ባለሙያ ተዘጋጅቶ መቅረብና የመረጃውን ተጠቃሚ ለውሳኔ የሚያበቃ መሆኑን ማረጋገጥ የግድ ይላል፡፡
ይህም ማለት ላለፉት 10 እና 20 ዓመታት ከ160 በላይ ሀገራት ድርጅቶች እየተገበሩት ያለ፣ ሀገራችን ኢትዮጵያም የዛሬ ስድስት ዓመት ገደማ በአዋጅ ያጸደቀችውና ይህንንም ለማስፈጸም የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኢዲት ቦርድ የሚባል መ/ቤት የተቋቋመለት ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ደረጃዎች የሚባል ፋይናንስ እና ፋይናንስ ነክ መረጃዎችን ለማቅረብ የሚያስችል ስርዓት መከተል የመጀመራችን ጉዳይ ነው፡፡
ይህ ስርዓት ሀገራችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያወጣችውን ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ (Home ገrown Economic reform) በመደገፍ የፋይናንስ ስርዓታችንን ጤናማነት ለማረጋገጥ ከሚያግዙን መሳሪያዎች ዋነኛውና ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ነው፡፡
የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድም በህግ የተጣለበትን ኃላፊነትና ተልዕኮ ለመወጣት በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ያለና የዘርፉ ውጤቶች እየታዩ ያሉ ቢሆንም በስርዓቱ አተገባበር ሂደት ከባለድርሻ አካላት ሚዲያው ዋነኛ መሆኑን በመረዳት በሀገራችን ያሉ በሁሉም ዘርፍ ለተሰማሩ የሚዲያ አካላት ይህን መድረክ ማዘጋጀቱ ከተልዕኮው ባለፊ ሀገራዊ ኃላፊነትን እንድንወጣ በማድረጉ ሊመሰገን ይገባል።
ክብራንና ክቡራት
ከዕለት ዕለት እንቅስቃሴያችን፣ ከዕድገትና ከውድቀታችን፣ከትርፍና ኪሳራችን፣ ከሰላምና ሁከታችን ወዘተ በስተጀርባ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ፋይናንስ አለ፡፡
ከፋይናንሱ በስተጀርባም በርካታ ተዋናዮች ያሉ ሲሆን እነዚህን ተዋናዮች በመግራት ውድቀትን ወደ ዕድገት ለመቀየር የሚያግዝ ይህን ከፍተኛ ጥራት ያለው የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ለማስፈጸም ከሚሰራ ተቋም ጋር በመስራት ህዝባችን ከዚህ የፋይናንስ መረጃ ተጠቃሚ መሆን የሚችልበትን የተጣራ መረጃ ተደራሽ ለማድረግ ይህ መልካም አጋጣሚ መሆኑን በመረዳት ሙያዊ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ አደራ እያልኩና እኛም የሚጠበቅብንን ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጂ መሆናችንን ቃል እየገባሁ መድረኩ ውጤታማ እንደሚሆን ባለሙሉ ተስፋ ነኝ፡፡
አመሰግናለው
Leave A Comment
You must be logged in to post a comment.