ታህሳስ 3 ቀን 2015 ዓ.ም

በአዲስ አበባ እና በዙሪያው ለሚገኙ የሒሳብ እና ለኦዲት ባለሙያዎች በሙሉ

ጉዳዩ፡-የስብሰባ ጥሪ ስለማድረግ

የኢትየጵያ ሒሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ለ2015/2016 የሂሳብ እና ኦዲት ሙያ የድርጅት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እድሳት ለማከናወን በዝግጅት ላይ መሆኑ ይታወቃል።

ስለሆነም ዕድሳቱን ለማከናወን የሚከፈለው የአገልግሎት ክፍያ በቴሌ-ብር ብቻ በመሆኑ በቴሌ-ብር አጠቃቀም ዙሪያ እና ኃላፊነቱ የተወሰነ ሽርክና ማህበር (LLP) አመሰራረት ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር ቦርዱ ለታህሳስ 06 ቀን 2015 ዓ.ም ዕቅድ ይዟል፡፡ በመሆኑም የሒሳብ እና የኦዲት አገልግሎት ለመስጠት በቦርዱ የተመዘገባችሁ ባለሙያዎች በተጠቀሰው ቀን በአዲስ አበባ በዲ-ሊዮፖል ሆቴል (ከባንቢስ ከፍ ብሎ በሚገኘው) ከጠዋቱ 3፡00 ላይ እንድትገኙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ማሳሰቢያ፡- በቀን 28/03/2015 ዓ.ም በተዘጋጀው መድረክ ላይ ስለቴሌብር አጠቃቀም ስልጠና የወሰዳቹሁ ኦዲተሮችን አይመለከትም።

 

የኢትየጵያ ሒሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ