ቀን፡-መስከረም10 ቀን 2014 ዓ.ም.

ማስታወቂያ

ጉዳዩ፡- አዲስ የሒሳብ እና ኦዲት ሙያ ፈቃድ ተግባራዊ መደረጉን ስለማሳወቅ

የኢትዮጵያ የሒሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ አዲስ የሙያ ፈቃድ በማውጣት በሒሳብ እና ኦዲት ሙያ ላይ መሰማራት ለሚፈልጉ እና በሙያው ላይ ለተሰማሩ አካላት ከመስከረም 01 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ አዲስ በፀደቀው “የሒሳብ እና የኦዲት ባለሙያዎች ፍቃድ አሰጣጥ እና የሒሳብ ሙያ ማህበራት ምዝገባ መመሪያ ቁጥር ኢሂኦቦ805/2013” መሠረት ብቻ ማስተናገድ የሚጀምር መሆኑን ያሳውቃል፡፡ በዚሁ መሰረት፡-

  • በቀድሞው አሰራር የሙያ ፈቃድ ለማውጣት አመልክታችሁ ማሟላት የሚገባችሁን መስፈርቶች እንድታሟሉ ተነግሯችሁ በሂደት ላይ ያላችሁ አካላት በአስቸኳይ እንድታሟሉ፣
  • አዲስ የድርጅት አመልካቾች እና የ2014 እድሳት ጠያቂዎች የድርጅት የሙያ ፈቃድ እድሳት የሚከናወነው በአዲሱ መመሪያ መሰረት መሆኑን እንድታውቁ እና
  • የግል የሙያ ፈቃድ አውጥታችሁ የድርጅት ፈቃድ ያላወጣችሁ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ እንድታወጡ እየገለፅን፣

ማሳሰቢያ፡- ከተጠቀሰው ዕለት ጀምሮ ያመለከቱ አመልካቾች የአገልግሎት ክፍያ ተመላሽ የማይደረግ መሆኑን እየገለፅን ህጉን ተግባራዊ በማያደርጉት ላይ ቦርዱ አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የኢትዮጵያ የሒሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ