- የተፈቀደለት ኦዲተር ሆኖ ለመስራት የሚያበቁ የትምህርት ደረጃ የሙያ ብቃትና የስራ ልምድ ሁኔታዎች የሚከተሉት መመዘኛዎች የሚያሟላ ግለሰብ የተፈቀደለት ኦዲተር /Authorized Auditor/ ሆኖ ለመስራት ማመልከት ይችላል፡፡
1.1. የታወቀ የአካውንቲንግ የሙያ ማህበር አባል የሆነና አባል ከሆነበት የሙያ ማህበር የስራ ምስክር ወረቀት/ Practicing certificate/ በኢትዮጵያ ውስጥ ሆኖ ያገኘ፣ እና አባል ከሆነ በኋላ 2 ዓመት በውጭ ኦዲተርነት የሰራ፡፡
1.2 የታወቀ የአካውንቲንግ የሙያ ማህበር አባል ሆኖ በሙያው ለመሰማራት የሚያስችለውን የስራ ምስክር ወረቀት /Practicing certificate/ ከኢትዮጵያ ውጭ ሆኖ ያገኘ ከሆነ፣
1.2.1 የስራ ምስክር ወረቀት /Practicing certificate/ ካገኘ በኋላ በውጭ ሀገር ከሁለት ዓመት ያላነሰ የስራ ልምድ በኦዲተርነት ካለው በኢትዮጵያ ውስጥ ቢያንስ የሶስት ወራት የስራ ልምድ በታወቀ የኦዲት ድርጅት ያለው ወይም፣
1.2.2 የስራ ምስክር ወረቀት / Practicing certificate / በውጭ ሀገር አግኝቶ ከ 1.5 እስከ ሁለት ዓመት ጊዜ በታወቀ የኦዲት ድርጅት ውስጥ ሲሰራ ቆይቶ የተመለሰ ከሆነ በኢትዮጵያ ውስጥ በታወቀ የኦዲት ድርጅት ውስጥ ቢያንስ ስድስት ወር የሰራ ልምድ ያለው ወይም፣
1.2.3 ከውጭ ሀገር የስራ ምስክር ወረቀት /Practicing certificate/ በውጭ ካገኘ በኋላ በውጭ ሀገር ምንም የስራ ልምድ ሳይኖረው ወይም በታወቀ የኦዲት ድርጅት ከአንድ ዓመት ላላነሰ ጊዜ ሲሰራ ቆይቶ የተመለሰ ከሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ በታወቀ የኦዲት ድርጅት ውስጥ ሁለት ዓመት የስራ ልምድ ያለው ወይም፣
1.2.4 ውጭ ሀገር እያለ የታወቀ የአካውንቲንግ የሙያ ማህበር አባል ሆኖ ምንም ሳይሰራ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ ኢትዮጵያ ውስጥ ሁለት ዓመታት ላላነሰ ጊዜ በታወቀ የኦዲት ድርጅት ውስጥ ሲሰራ ቆይቶ የስራ ምስክር ወረቀት / Practicing certificate / ፣ያገኘ
1.3 የተፈቀደለት ኦዲተር ለመሆን የሚያበቁ ሌሎች ሁኔታዎች የተፈቀደለት ኦዲተር የኦዲት ድርጅት አቋቁሞ በግል ለመሰራት ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ የሚከተሉት ማሟላት ይኖርበታል፣
1.3.1 በሙያው ብቁ የሆኑ ሠራተኞችን በቋሚነት ቀጥሮ ማሰራትና ቢያንስ አንድ ቡድን በስራው ላይ ማሠማራት የሚችል፣
1.3.2 አስፈላጊ ቢሮና ልዩ ልዩ ለስራው የሚያገለግሉ የቢሮ ቁሳቁሶችን የሚያሟላ፣
1.3.3 አስፈላጊ የሆኑ ልዩ ልዩ የመድን ዋስትናዎችን ያሟላ፣
1.3.4 የተፈቀደለት ኦዲተር ሆኖ ለመስራት ከሚከተለው የመንግስት አካል ተገቢ የንግድ ፍቃድ ሊኖረው ይገባል፣
- 2. የተፈቀደለት የሂሳብ አዋቂ ሆኖ ለመስራት የሚያበቁ የትምህርት ደረጃ፣ የሙያ ብቃት የስራ ልምድ ሁኔታዎች የሚከተሉትን መመዘኛዎች የሚያሟላ ማንኛውም ግለሰብ የተፈቀደለት የሂሳብ አዋቂ /Authorized Accountant/ ሆኖ ለመስራት ማመልከት ይችላል፡፡
2.1 የታወቀ የአካውንቲንግ የሙያ ማህበር አባል የሆነ ፣ ወይም
2.2 ከታወቀ ዮኒቨርስቲ በሂሳብ አያያዝ በማስተር ወይም በዶክትሬት ዲግሪ ከተመረቀ በኋላ በጥምር የሂሳብ አያያዝ /Double entry accounting/ በሚጠቀሙ መ/ቤቶች ውስጥ 4 ዓመት በፋይናንስ /በአካውንቲንግ ወይም በኦዲተርነት የስራ ሀላፊነት ደረጃ የሰራ፣ ወይም
2.3 ከታወቀ ዮኒቨርስቲ በሂሳብ አያያዝ በባችለር ዲግሪ ከተመረቀ በኋላ በጥምር የሂሳብ አያያዝ /Double entry accounting/ በሚጠቀሙ መ/ቤቶች ውስጥ 8 ዓመት በፋይናንስ/በአካውንቲንግ ወይም በኦዲተርነት የስራ ልምድ ያለውና ከዚህ ውስጥ ቢያንስ አራቱን ዓመታት በፋይናንስ/በአካውንቲንግ ወይም በኦዲተርነት ስራ በሀላፊነት ደረጃ የሰራ፣ ወይም
2.4 ከታወቀ ዮኒቨርስቲ በሂሳብ አያያዝ በባችለር ዲግሪ ከተመረቀ በኋላ የአካውንቲንግ ባችለር ዲግሪ በሚሰጡ በታወቁ ዮኒቨርስቲዎች ውስጥ 12 ዓመታት የአካውንቲንግ ኮርሶችን ያስተማረ እና በተጨባጭ በጥምር የሂሳብ አያያዝ /Double entry accounting/ በሚጠቀሙ መ/ቤቶች ውስጥ ቢያንስ ከአንድ ዓመት ላላነስ ጊዜ በፋይናንስ/በአካውንቲንግ ስራ የሰራ፣ ወይም
2.5 የፋይናንስ/የአካውንቲንግ ስራ በሰራባቸው ድርጅቶች ሂሳብ በመዝጋት የተሳተፈበትንና የተዘጋና በኦዲተር የተመረመረ ሂሳብ የሚያቀርብ፣
2.6 ከላይ በተራ ቁጥር 2.5 የተመለከተው በኦዲተርነት የሰሩትንና የተፈቀደለት የሂሳብ አዋቂ ሆኖ ለመስራት የሚያመለክቱትን አይመለከትም፡፡
- 3. ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ለማግኘት አመልካቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡-
2.1 የትምህርት፣ የአገልግሎትና ሌሎች አስፈላጊ ማስረጃዎችና ኦሪጅናልና በተወሰነው ልክ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
2.2 ማመልከቻ ከአንድ ጉርድ ፎቶግራፍ ጋር፡፡
2.3 የቀበሌ ነዋሪነት መታወቅያ
5.4 በማህበራዊ ኑሮ ውስጥ መልካም ስነ-ምግባር ያለው፣ በፍርድ ቤት መብቱ ያልተገፋፋ ሆኖ፣ ቀደም ሲል ከሰራባቸው መ/ቤቶች የአገልግሎት የምስክር ወረቀት ያለው፣
5.5 የውጭ አገር ዜጋ በኢትዮጵያ በግል የሂሳበ አዋቂነት ለመስራት ሲያመለክት የስራ ፍቃድና የነዋሪነት ማስረጃ ያለው መሆኑ ተረጋግጦ ከፍ ብሎ በተዘረዘሩት መስፈርቶች አንዱን ሲያሟላ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሊሰጠው ይችላል፡፡
5.6 ከሶስት ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ስለግለሰቡ የሚያወቁ የምስክርነት ወረቀት፣
5.7 ከተፈቀደለት ኦዲተር ወይም የተፈቀደለት ሂሳብ አዋቂ የብቃት ማረጋገጫውን በሚወስድበት ወቅት ከሚሰራበት ድርጅት የስራ መልቀቂያ ማስረጃ፣
5.8 ማንኛውም የተፈቀደለት ኦዲተር ወይም የሂሳብ አዋቂ በተሰጠው የሙያ ዘርፍ ብቻ መስራት ይጠበቅበታል፡፡
5.9 እድሜው ከ25 ዓመት ያላነሰ፣
5.10 ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎች፡
Leave A Comment
You must be logged in to post a comment.