ማስታወቂያ

ከክልል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የሒሳብ እና የኦዲት ፈቃድ ለተሰጣችሁ ባለሙያዎች

ለሒሳብ እና ኦዲት ባለሙያዎች ፈቃድ የመስጠት፣ የማደስ እና የመቆጣጠር ሥልጣን ለክልል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በውክልና ተሰጥቶ የነበረ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን ከየካቲት 16 ቀን 2014 ዓ/ም ጀምሮ ውክልናው የተነሳ በመሆኑ ፍቃድ የመስጠት፣ የማደስ እና ባለሙያዎችን የመቆጣጠር ተግባር በኢትዮጵያ የሒሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ተጨማሪ መረጃ አዲስ ዘመን ጋዜጣ 82ኛ እትም ቁጥር 208 መጋቢት 28 ቀን 2015 ዓ/ም እትም ማግኘት ይችላሉ፡፡