ከዓለም ባንክ ልዑክ ጋር ውይይት ተካሄደ
*******************************************************
የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ አመራሮች ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር የEthiopia Governance Advisory & Technical support ፕሮጀክት ትግበራ ላይ ከሚመለከታቸው የዓለም ባንክ ተወካዮች ጋር የካቲት 27 ቀን 2015 ዓ.ም. ተወያዩ፡፡
የውይይቱ ዋነኛ ዓላማ በኢትዮጵያ በመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተግባራዊ እየተደረገ ያለውን የሂሳብ ሪፖርት አዘገጃጀት እና አቀራረብ ደረጃዎች ውጤታማ ለማድረግ የሪፖርት አቅራቢ አካላትን የፋይናንስ ሓላፊዎች፣ የፋይናንስ ባለሙያዎች፣ የሂሳብ እና ኦዲት ባለሙያዎች እንዲሁም የቦርዱን እና ሌሎች ተቆጣጣሪ አካላትን ባለሙያዎች አቅም ለማዳበር የታቀደ መሆኑን የቦርዱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሂክመት አብደላ አስረድተዋል፡፡
ፕሮጀክቱ ከ የካቲት 27 እስከ መጋቢት 8 ቀን 2015 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተዘጋጀው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እንደሚከናወን እና ከመድረኩ የተሻለ ውጤት እንደሚጠበቅም ለማወቅ ተችሏል፡፡


Leave A Comment
You must be logged in to post a comment.