ቀን 10/4/2015
ለሚመለከተዉ ሁሉ
የተሰረዘ የሙያ ፈቃድ ምዝገባ የምስክር ወረቀትን ይመለከታል፡፡
ከኢትዮጵያ ሒሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ የሙያ ፈቃድ የምዝገባ የምስክር ወረቀት የወሰደ ማንኛውም የሒሳብ/የኦዲት ባለሙያ የምስክር ወረቀቱን ማሳደስ ከሚገባው ጊዜ ጀምሮ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ካላሳደሰ በሒሳብ እና ኦዲት ባለሙያዎች ፍቃድ አሰጣጥ እና የሒሳብ ሙያ ማኅበራት ምዝገባ መመሪያ ቁጥር 805/2013 አንቀጽ 6(4) መሠረት የምዝገባ የምስክር ወረቀቱ እንደሚሰረዝ ተደንግጓል፡፡ በዚህም መሰረት፡-
1ኛ. ዳግም ደሳለኝ ገደቡ የተፈቀደለት የሂሳብ አዋቂ ድርጅት የምዝገባ ምስክር ወረቀት ቁጥር ACF-00374 እና
2ኛ. ፍቅሩ በቀለ አበበ የተፈቀደለት የሂሳብ አዋቂ ድርጅት የምዝገባ ምስክር ወረቀት ቁጥር ACF00055 የምስክር ወረቀታቸውን ሳያስድሱ አንድ ዓመት ያለፋቸው በመሆኑ ከ ነሐሴ 28/2014 ጀምሮ የምዝገባ የምስክር ወረቀታቸው የተሰረዘ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ስለሆነም በተጠቀሱት የሒሳብ አዋቂ ድርጅቶች ስም የሒሳብ ሥራ ተሰርቶ ቢገኝ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እናሳስባለን፡፡
የኢትዮጵያ ሒሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ
Leave A Comment
You must be logged in to post a comment.