የአይ ኤፍ አር ኤስ 17 የኢንሹራንስ ውል የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ፡፡
**************************************************************************************
የኢትዮጵያ የሒሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ ከመጋቢት 4-5/2015 ዓ.ም. ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የአይ ኤፍ አር ኤስ 17 ስታንዳርድ የኢንሹራንስ ውሎች ትግበራ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በዲ-ሌኦፖል ሆቴል ለኢንሹራንስ ኩባንያ ባለሙያዎች እና ለሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ የቴክኒክ አባላት ተሰጠ፡፡
በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቦርዱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሂክመት አብደላ የመድረኩ ዋና ዓላማ እ.ኤ.አ ከጃኑዋሪ 1 ጀምሮ የሚተገበረውን የአይ ኤፍ አር ኤስ 17 ስታንዳርድ ውልን በተመለከተ የአቅም ግንባታ ስራ መሰራት በማስፈለጉ መድረኩ ከኢንሹራንስ ውል ሰጭ ማህበራት በጋራ በዘርፉ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የሚሰጥ በመሆኑ ተሳታፊዎች የአይ ኤፍ አር ኤስ 17 ውል ስታንዳርድ ትግበራውን ውጤታማ ለማድረግ ግንዛቤ እንዲያገኙ ማስቻል መሆኑ ተገልጿል፡፡
በመድረኩ የአይ ኤፍ አር ኤስ 17 ስታንዳርድ ውል ጽንሰ-ሃሳብ በተመለከተ ማብራሪያ ተሰጥቶ አተገባበሩን እና ተግዳሮቶችን በማንሳት በተሳታፊዎች ጥያቄ እና መልስ፣ የቡድን ውይይት ተካሄዷል፡፡
ዓለም ዓቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀት ደረጃዎች /አይ ኤፍ አር ኤስ/ ስታንዳርድ ትግበራ ስንጀምር ቦርዱ አስፈላጊ ስልጠናዎችን በመስጠት፣ ተገቢ የሆነ ድጋፍ እና ክትትል ተደርጎላቸው መተግበር መቻላቸውን የኢንሹራንስ ውል ሰጭ ማህበራት ተወካይ የሆኑት ወ/ሮ እመቤት አለማየሁ ገልጸዋል፡፡
የአይ ኤፍ አር ኤስ 17 ስታንዳርድ ውል ስልጠና ባለፈው ሳምንት ለኦዲተሮች በተመሳሳይ መሰጠቱ ይታወሳል፡፡
Leave A Comment
You must be logged in to post a comment.