የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ የአገራችንን ፌደራላዊ አደረጃጀት የተከተለ ጠንካራ ሀገር አቀፍ የአካውንቲንግና ኦዲት ሙያ ማህበር እንዲመሰረት በፌደራል እና በክልል ከሚገኙ የሙያ ማህበራት፤ከዓለም አቀፉ የአካውንታንቶች ፌዴሬሽን እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

 

በዚህም መሰረት አገር አቀፍ የሙያ ማህበር የማደራጀት ሂደቱን ለማገዝ ከዓለም አቀፉ የአካውንታንቶች ፌዴሬሽን (IFAC)ከተላከ  ባለሙያ ጋር በመተባበር  በአገራችን  ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር የዳሰሳ ጥናት  ለማድረግ ያቀደ ሲሆን ለግማሽ ቀን  በሙያ ማህበሩ ምስረታ ዙሪያ ለመወያየት ፍላጎት ያላችሁ ባለሙያዎች ጳጉሜ 2 ቀን 2009 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር አዳራሽ በመገኘት እንድትሳተፉ እና ያላችሁን አስተያየት እንድትሰጡ  ቦርዱ ጥሪውን ያቀርባል፡፡