የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ የጋራ ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ!
የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ከኦሮሚያ ክልል የሂሳብ አያያዝ ባለሙያዎች ማህበር ጋር ሚያዚያ 19 ቀን 2009 ዓ.ም የጋራ የስምምነት ሰነድ በቦርዱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተፈራረመ፡፡ የስምምነቱ ዋና ዓላማ በክልሉ ውስጥ የሚገኘውን የሙያ ማህበር አቅም በመገንባትና የአለምአቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብን ተግባራዊ በማድረግ በዋናነት የህዝብ ጥቅምን ለማስከበር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መሆኑ ተገልጿል፡፡ የጋራ ስምምነቱም በክልሉ [...]