ቦርዱ የIFRS አተገባበርን አስመልክቶ በሐረር ከተማ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጠ!
የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ በአለምአቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ (IFRS) አተገባበር ላይ ግንቦት 14 ቀን 2009 ዓ.ም በሀረር ከተማ ወንደርላንድ ሆቴል የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጠ፡፡ በግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሙ ላይ ከሐረሪ ክልላዊ መንግስት፤ ከድሬደዋ ከተማ አስተዳደር እና ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልላዊ መንግስት የተውጣጡ ዋና ኦዲተሮች፤ የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊዎች፤ የገቢዎችና ጉምሩክ ኃላፊዎች፤ የመንግስት የልማት ድርጅቶች የአካውንቲንግ ሙያ [...]