Monthly Archives: August 2017

Home/2017/August

ለኦዲተሮች በሙሉ የስብሰባ ጥሪ

የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ በዓለምአቀፍ የኦዲት ደረጃዎች ዙሪያ እና በኦዲተሮች የመስክ ምልከታ ላይ በተገኙ ግኝቶች ላይ ውይይት ማድረግ ስላስፈለገ እንዲሁም ስለወደፊቱ አቅጣጫ ማስቀመጥ ይቻል ዘንድ በነሀሴ 24 ቀን 2009 ዓ.ም በገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር አዳራሽ ለግማሽ ቀን የሚቆይ ስብሰባ ላይ እንድትገኙ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

By |2017-08-28T13:20:37+00:00August 28th, 2017|ማስታወቂያ|0 Comments

የብረታብረት እና ኢንጀነሪንግ ኮርፖሬሽን የIFRS ትግበራን በማካሄድ በአርአያነቱ የሚጠቀስ ሥራ መስራቱ ተገለጸ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የብረታብረት እና ኮርፖሬሽን ከኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ጋር በመተባበር የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀት እና አቀራረብ ደረጃዎች (IFRS)ን በመተግበር አመርቂ ሥራ በማከናወን ላይ እንደሚገኝ በኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ዋና ዳይሬክተር የሚመራ ቡድን አስታወቀ፡፡ ሃምሌ 26 ቀን 2009 ዓ.ም ኮርፖሬሽኑ ከትግበራ ጋር ተያይዞ እያከናወነ ያለውን ሥራ የተመለከተው የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ቡድን፤ [...]

By |2017-09-02T11:12:38+00:00August 25th, 2017|ዜና|0 Comments

ለመቐለ ዩኒቨርሲቲ የአካውንቲንግና የፋይናንስ መምህራን በIFRs ላይ ያተኮረ የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጣቸው

የመቐለ ዩኒቨርስቲ የአካውንቲንግና የፋይናንስ መምህራን በዓለምአቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ደረጃዎች (IFRs) ላይ ያተኮረ የአሰልጠኞች ስልጠና ተሰጣቸው፡፡ ከሃምሌ 27 ቀን እስከ ነሐሴ 7 ቀን 2009 ዓ.ም በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ በተሰጠው ስልጠና 30 የመቐለ ዩኒቨርስቲ መምህራን ተሳትፈውበታል፡፡ ስልጠናው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአካውንቲንግና የፋይናንስ የትምህርት ክፍል በተውጣጡ መምህራን ተሰጥቷል፡፡ ለ11 ቀናት ያህል በተሰጠው የአሰልጣኞች ስልጠና [...]

By |2017-09-02T11:15:24+00:00August 25th, 2017|ዜና|0 Comments

አዲስ የኦዲት አንዲሁም የሂሳብ ሙያ ፈቃድ ለማውጣት የተቀመጡ መስፈርቶች፤፤

የተፈቀደለት ኦዲተር ሆኖ ለመስራት የሚያበቁ የትምህርት ደረጃ የሙያ ብቃትና የስራ ልምድ ሁኔታዎች የሚከተሉት መመዘኛዎች የሚያሟላ ግለሰብ የተፈቀደለት ኦዲተር /Authorized Auditor/ ሆኖ ለመስራት ማመልከት ይችላል፡፡ 1.1.  የታወቀ የአካውንቲንግ የሙያ ማህበር አባል የሆነና አባል ከሆነበት የሙያ ማህበር የስራ ምስክር ወረቀት/ Practicing certificate/ በኢትዮጵያ ውስጥ ሆኖ ያገኘ፣ እና አባል ከሆነ በኋላ 2 ዓመት በውጭ ኦዲተርነት የሰራ፡፡ 1.2 የታወቀ [...]

By |2017-08-24T11:08:12+00:00August 24th, 2017|ማስታወቂያ|0 Comments

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር IFRS ን ያካተተ የአካውንቲንግና ፋይናንስ ትምህርት የካሪኩለም ክለሳ ውይይት አካሄደ!

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ነሐሴ 13 ቀን 2009 ዓ.ም ዓለምአቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ደረጃዎች (IFRSs)ን ያካተተ የካሪኩለም ክለሳ ከሀገሪቱ የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከተውጣጡ መምህራን ጋር ውይይት አካሄደ፡፡  ውይይቱ የተካሄደው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በማንዴላ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ሲሆን፤ 116 ያህል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ክፍል ኃላፊዎችና መምህራን በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተዋል፡፡ የአዲስ [...]

By |2017-09-02T11:17:59+00:00August 21st, 2017|ዜና|0 Comments

ቦርዱ በአማራ ክልል ከሚገኙ  የመንግስት የልማት ድርጅት አመራሮች ጋር ውይይት አካሄደ!

በኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ዋና ዳይሬክተር የተመራ ቡድን በአማራ ክልል ከሚገኙ የመንግስት የልማት ድርጅት አመራሮች ጋር በአለምአቀፍ የፋይናስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ደረጃዎች (IFRSs) አተገባበር ላይ ከነሐሴ 4 እስከ ነሐሴ 5 ቀን/2009 ዓ.ም ለሁለት ቀናት ያህል ውይይት አካሄደ፡፡ ውይይቱ በዋናነት በክልሉ በሚገኙና ለክልሉ ተጠሪ ለሆኑ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ከሰኔ 30 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ በሀገር [...]

By |2017-09-02T11:24:59+00:00August 21st, 2017|ዜና|0 Comments

ቦርዱ በአማራ ክልል ከሚገኙ የሂሳብና ኦዲት ባለሙያዎች  ጋር ውይይት አካሄደ!

                  በኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ  ዋና ዳይሬክተር የተመራ ቡድን አማራ ክልል ከሚገኙ የሂሳብ እና ኦዲት ባለሙያዎች ጋር ሃምሌ 3 ቀን 2009 ዓ.ም ውይይት አካሄደ፡፡ በውይይቱ ላይ የቦርዱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጋሼ የማነ ከክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ፍቃድ ከተሰጣቸው የክልሉ የሂሳብና ኦዲት ባለሙያዎች ጋር ከቦርዱ የወሰዱትን ፈቃድ [...]

By |2017-09-02T11:32:05+00:00August 21st, 2017|ዜና|0 Comments

የኢትዮጵያ የማይክሮፋይናንስ ተቋማት ማህበር የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠው

የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ከሐምሌ 24 ቀን እስከ ነሐሴ 1 ቀን 2009 ዓ.ም ከተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች ለተወጣጡ የማይክሮፋይናንስ ሰራተኞች አለምአቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ደረጃዎች (IFRS)ን የተመለከተ የአሰልጣኞች ስልጠና በአዳማ ከተማ ሰጥቷል፡፡ በስልጣናው ከየተቋማቱ የተውጣጡ 70 ያህል የሂሳብ ባለሙያዎች እንደተሳተፉ የተገለጸ ሲሆን፤ ስልጠናው በዘርፉ የሚታየውን የባለሙያዎች እጥረት የሚያቃልልና ወደ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና [...]

By |2017-08-16T04:41:28+00:00August 16th, 2017|ዜና|0 Comments

ለኦሞና ለሲዳማ የማይክሮፋይናንስ ተቋማት ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ

  የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ከሐምሌ 16 እስከ ሐምሌ 27 ቀን 2009 ዓ.ም ለአስር ቀናት ያህል በዓለምአቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ደረጃዎች (IFRS) ላይ ያተኮረ የተግባር ሰልጠና ለኦሞና ለሲዳማ ማይክሮፋይናንስ ሰራተኞች በይርጋለም ከተማ ስልጠና ሰጠ፡፡ ስልጠናው የአዲሱን የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ አዋጅ 847/2006 መተግበር የሚችሉ የሂሳብ ባለሙያዎች ለማፍራት፣ አቅማቸውን ለማዳበርና ትግበራውን አጠናክሮ ለማስቀጠል ትኩረት [...]

By |2017-08-16T04:39:54+00:00August 16th, 2017|ዜና|0 Comments

ለግብር ከፋዮች በሙሉ

  የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ በአዎጅ ቁጥር 847/2006 አንቀፅ 4 (2)(መ) የሪፖርት አቅራቢ አካላትን የህዝብ ጥቅም ያለባቸው ወይም አነስተኛና መካከለኛ በሚል መለየት የሚያስችል መስፈርቶችን በማውጣት  እነዲመዘግብ ስልጣን የተሰጠው መሆኑ ይታወቃል፡፡ እንዲሁም ደግሞ በአንቀፅ 8 (1) እና 4(2)(ሸ) ማንኛውም ሪፖርት  አቅራቢ አካል ቦርዱ በሚያወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የሂሳብ መግለጫውን ለቦርዱ  ማቅረብ [...]

By |2017-08-05T09:30:03+00:00August 5th, 2017|ማስታወቂያ|0 Comments