ለቦርዱ አዲስ ዋና ዳይሬክተር ተመደበለት
ክብርት ወ/ሮ ሂክመት አብደላ አብዱልመሊክ ከጥቅምት 20 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድን በዋና ዳይሬክተርነት እንዲመሩ በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር በክቡር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በተጻፈ ደብዳቤ ተመደቡ፡፡ ክብርት ዋና ዳይሬክተሯ ጥቅምት 24 ቀን 2012 ዓ.ም. ከቦርዱ የሥራ ኃላፊዎች ጋር የሥራ ትውውቅ ባደረጉበት ወቅት የሀገሪቱን የፋይናንስ ሥርዓት ጤናማነት በማረጋገጥ የድርጅቶችን የውድቀትና ኪሳራ ስጋት ለመቀነስ [...]