ለታክስ ሥርዓቱ ውጤታማና ጤናማነት የዘርፉ ተቆጣጣሪና ሙያተኞች ሚና ጉልህ ነው
የኢትየጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ የኢፌዲሪ ገቢዎች ሚኒስቴር ባዘጋጀው የታክስ አስተዳደር መመርያ ቁጥር 152/2011ዓ.ም አተገባበር ላይ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ማክሰኞ ነሀሴ 21 ቀን 2011ዓ.ም በገቢዎች ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት አደረገ። በእለቱም ክቡር አቶ ዘመዴ ተፈራ የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የታክስ አስተዳደሩን ማዘመን፣ጤናማና ውጤታማ ማድረግ መንግስት ከጀመራቸው ሁለንተናዊ ለውጦች (Reforms) [...]