ህግ ጥሰው የሙያ ስራ ላይ በተሰማሩ ሙያተኞች ላይ እርምጃ ተወሰደ

የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ከቦርዱ ህጋዊ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ እና የግልና የድርጅት የሙያ ፈቃድ ወስደው ግን ሳያድሱ በቀሩ እና ባልታደሰ የሙያ ፈቃድ የሂሳብ ስራዎች በሰሩ የሂሳብ እና የኦዲት ሙያተኞች ላይ ህጋዊ እርምጃ ወሰደ፡፡ ቦርዱ የሂሳብ አያያዝና የኦዲት ሙያን ለመቆጣጠር በተሰጠው ኃለፊነት ላይ ተመስርቶ ጠንካራ የምርመራና የህግ ማስከበር ስርዓትን በማስፈን በኢትዮጵያ ውስጥ የሙያውን ተአማኒነት ለመገንባት [...]