ለፋይናንስ ሪፓርት አቅራቢ አካላት በሙሉ
ዓለም ዓቀፍ የፋይናንስ ሪፓርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ደረጃዎች (IFRS, IFRS for SMEs and IPSAS) ትግበራ የኢትዮጽያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ባስቀመጠው የትግበራ ፍኖተ-ካርታ መሰረት እየተከናወነ ይገኛል፡፡ ሁሉንም መስፈርቶች የሚያሟሉ አካላትም በወቅቱ በቦርዱ በአካል በመገኘት ወይም በመንግስት የኤሌክትሮኒክ አገልግሎት (e-service) በመጠቀም ድርጀታቸውን አስመዝግበው ለድርጀታቸው የሚገባውን ደረጃ እየተገበሩ ይገኛሉ፡፡ ከፍተኛ የህዝብ ጥቅም ያለባቸው ሪፖርት አቅራቢ አካላት ከ2010 ዓመት [...]