የኢትዮጵያ የሒሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ በፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀት እና አቀራረብ አዋጅ ቁጥር 847/2006 አንቀጽ 4(2)(ሀ) እና 53(2) በተሠጠው ሥልጣን መሠረት የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ደረጃዎች አተገባበርን ተከትሎ ከሚደረግ የኃብት ትመና ወይም ማስተካከያ የሚገኝ ለውጥ በሚመመለከት የአፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 985/2016 አውጥቷል፡፡ በመሆኑም ማንኛውም ሪፖርት አቅራቢ አካል ከኃብት ትመና ወይም ማስተካከያ የሚገኘውን ጭማሪ ወደ ጥሬ ገንዘብ ያልተቀየረ እና የማይመነዘር ትርፍ በመሆኑ ለዋና ገንዘብ ማሳደጊያነትም ሆነ ለትርፍ ድርሻ ክፍፍል ማዋል አይችልም፡፡ ስለሆነም ከኃብት ትመና ወይም ማስተካከያ የሚገኘውን ጭማሪ ከሌላ ሊከፋፈል ከሚችል የተጣራ ኃብት ተለይቶ መመዝገብ ያለበት በመሆኑ ሪፖርት አቅራቢ አካላት ከመመሪያው ጋር አባሪ በተደረገው ማብራሪያ እና ምሳሌ መሠረት ተግባራዊ እንድታደርጉ እንመክራለን፡: