IFRS ካልተገበሩ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ጋር ውይይት ተካሄደ

 የኢትዮጵያ ሂሰብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ካልተገበሩ አምስት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የትግበራ ባለሙያዎች ጋር ግንቦት 2 እና 3 ቀን 2014 ዓ.ም ተወያየ፡፡

በዕለቱም የቦርዱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ አጎናፍር እንደተናገሩት ቦርዱ ቀድሞ ባወጣው የደረጃዎች የትግበራ ፍኖተ ካርታ መሠረት የመንግስት የልማት ድርጅቶች የመጀመሪያዎቹ ተግባሪዎች ተደርገው ቢለዩም ተግብረው ወደ ቦርዱ ያቀረቡት ጥቂት መሆናቸውን ገልጸው በወቅቱ አለመተግበር ግን ህግን ካለማክበርም አልፎ የድርጅቶችን የፋይናንስ እና ፋይናንስ ነክ እንዲሁም ተያያዥ መረጃዎችን ለተጠቃሚው እንዳይደርሱ ማድረግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በውይይቱም ተቋማቱ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ደረጃዎችን ለመተግበር ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው ቢሆንም የአመራሮች መቀያየር፣ የግልጽነትና ቁርጠኝነት መጓደል እና የመሳሰሉትን ተግዳሮቶች ቢያነሱም ከመድረኩ ባገኙት ምክረ-ሃሳብ ከወዲሁ ወደ ዝግጅት ሊያስገባቸው እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

ውይይቱን የቦርዱ የሙያ አማካሪ አቶ አሸናፊ ጌታቸው የመሩት ሲሆን በዘርፉ የካበተ ልምድ ያላቸው ሁለት የውጭ ሀገር ባለሙያዎች በበይነ-መረብ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡